ሰበር መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡጁንቡራ ላይ በአሸባሪ ችግር ገጠመው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡጁምቡራ በአሸባሪነት በተጠረጠረ ግለሰብ ችግር ገጠመው በቡጁምቡራ ያረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላንአንድ ተሳፋሪ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት በሰነዘረው ማስፈራሪያ አውሮፕላኑ ወታደራዊአውሮፕላኖች ወደሚያርፉበት የቡጁምቡራ አየር ማረፊያ እንዲቆም መደረጉ ተነገረ።

አውሮፕላኑ ዛሬ በቀጥታ በረራ ከአዲስ አበባ ወደ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ እየበረረ ሳለ ነበር ችግሩየተከሰተው ተብሏል።

ቢቢሲ ስማቸው እንዳይጠቀስ ከጠየቁ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ለማረጋገጥ እንደቻለው የተባለው ችግርእንዳጋጠመና ምንም ጉዳት ሳይደርስ ቡጁምቡራ አርፏል።

ቢቢሲ ክስተቱን በተመለከተ ለማጣራት ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ክፍል ደውሎ ጥያቄቢያቀርብም የተሰጠው ምላሽ ስለጉዳዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ መግለጫ እንደሚሰጥ ብቻ ነው።

ነገር ግን መረጃ የተጠየቁት የአየር ባልደረባ ስለክስተቱ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበው ማረጋገጫም ሆነማስተባበያ ለመስጠት አልፈቀዱም።

ክስተቱን በተመለከተ ለቢቢሲ ያረጋገጡት የአየር መንገዱ ባልደረባ እንደሚሉት ከሆነ “አውሮፕላኑ በአየርማረፊያው ወታደራዊ ክፍል ውስጥ እንዲያርፍ ተደርጎ ችግሩን የፈጠረው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል።”

ቢቢሲ ከተጓዦቹ አንዱን በማነጋገር እንዳረጋገጠው ክስተቱ ተሳፋሪዎች ላይ ጭንቀት ፈጥሮ ነበር።

ነገር ግን በአውሮፕላኑ ውስጥ ያጋጠመውን ችግር የፈጠረው ግለሰብ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀነገር የለም።

የቡሩንዲ የደህንነት መስሪያ ቤት በትዊተር ገጹ ላይ ስለክስተቱ ጠቅሶ በሽብር ድርጊት የተጠረጠረው ግለሰብምበቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክቷል።

ክስተቱን በተመለከተ ቢቢሲ ያገኘውና እስካሁን በሁለተኛ ወገን ያልተረጋገጠው መረጃ እንደሚያመለክተውግለሰቡ በአውሮፕላኑ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት አውሮፕላኑን እንደሚያፈነዳው በመግለጽበማስፈራራቱ ችግሩ መከሰቱ አመልክቷል።

ከዚህ አንጻር ለቢቢሲ የተናገሩት የአየር መንገዱ ባልደረባ ክስተቱ በሰላም መጠናቀቁንና በተሳፋሪዎችም ሆነበአውሮፕላኑ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል።

በእርግጥ ግለሰቡ እንዳለው የሚፈነዳ ነገር ይዞ እንደነበረ የሚያመለክት ነገር ያልተገኘ ሲሆን፤ ለፈጸመውድርጊትም ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን ምንም የታወቀ ነገር የለም።

አውሮፕላኑ ምን ያህል ተጓዦችን አሳፍሮ እንደነበረና ችግሩ የተከሰተው ለማረፍ በተቃረበበት ይሁን ወይም በጉዞላይ እንዳለ አልታወቀም።

ክስተቱን ተከትሎ አውሮፕላኑ በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኝ የወታደራዊ አውሮፕላኖች ማቆሚያ ክፍልእንዲቆይ እንደተደረገ ምንጮች ከቡጁምቡራ አመልክተዋል።

የእስራኤል የልብ ህክምና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ህክምና ሊሰጡ ነው

መቀመጫውን እስራኤል ያደረገው ‘ሴቭ ኤ ቻይልድ’ስ ኸርት የተባለና ለትርፍ ያልተቋቋመው አለም አቀፍ የልብ ህክምና ቡድን ነገ በኢትዮጵያ የልብ ህከምና ማዕከል አገልግሎቱን ይሰጣል።ቡድኑ ለ30 ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና እና ሌሎች ተያያዥ ህክምናዎችን እንደሚሰጥ ፒአር ኒውስ ከዋሽንግተን ዘግቧል።

‘የህፃናትን ልብ ማዳን’ የሚል ተልዕኮ ያነገበው ቡድን በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ከሚሰሩትና የቡድኑ አጋር ከሆኑት ዶክተር ያየህይራድ መኮንን ጋር በመሆን በማዕከሉ ህክምናውን ይሰጣል ተብሏል።የቡድኑ አባላት በቆይታቸው ለህፃናት ቅድመ ምርመራ የሚያደርጉ ሲሆን ከዚህ በፊት ህክምና ያገኙ ክትትል ይደረግላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ በኢትዮጵያ ስራ የጀመረበትን 25 አመት ባለፉት ዓመታት በቡድኑ ህክምና ያገኙ 700 ኢትዮጵያውያን ህፃናት በተገኙበት ይከበራል።

ቡድኑ በመላው አለም ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖትና ዜግነት ሳይለይ የህፃናትን ልብ ለማከም ይሰራል” ሲሉ የተቋሙ ዋና ተጠሪ ሲሞን ፊሸር ተናግረዋል።

“በኢትዮጵያ የምናከናውነው ተልዕኮ ዘመኑ የሚጠይቃቸውን የልብ ህክምና ቁሳቁስ ከማሟላት አንስቶ፣ ላቦራቶሪ፣ ዘመናዊ የቀዶ ጥገና ክፍል እና የጽኑ ህክምና ክትትል ለማድረግ የሚያግዙ ባለሙያዎችንና ቁሳቁሶችን ማቅረብን ይጨምራል” ብለዋል።

በዚህም አገልግሎቱን የሚፈልጉ ህፃናትን ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል ገልጸው፤ ”በኢትዮጵያ የምናከናውነው ተልዕኮ የብዙ ልጆችን ህይወት የለወጠ ሲሆን በቡድናችንና በአጋሮቻችን ተግባር በእጅጉ እንደሰታለን” ብለዋል።

‘ሴቭ ኤ ቻይልድ’ስ ኸርት’ በኢትዮጵያ ዘጠኝ የልብ ህክምና ስፔሻሊስቶችን አሰልጥኗል። ዘጠኙም ባለሙያዎቹ አሁን ላይ በአገራቸው ህክምናውን እየሰጡ እንደሚገኙም ተገልጿል።ተቋሙ ከተቋቋመበት አ.አ.አ 1995 አንስቶ በ62 አገሮች ለሚገኙ 5 ሺ ህፃናት የልብ ህክምና ሰጥቷል።

ምንጭ:- ኢዜአ

ከፅዳት ሠራተኝነት እስከ አብራሪነት

ከወደ ናይጄሪያ የተሰማ የአንድ ስኬ ታማ ግለሰብን ታሪክ ልናስነብባችሁ ወደናል። ኢንተለጀንስ ዶት ኮም እንዳስነበበው ግለሰቡ አብራሪ የመሆን ህልሙን የጀመረው ከአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ተነስቶ ሲሆን አሁን ላይ የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ለመሆን በቅቷል። የዚህ ስኬታማ ሰው አጭር የስኬት ታሪክ እንደሚከተለው ነው።

ናይጀሪያዊው መሀመድ አቡበከር ከዛሬ 24 አመታት በፊት የአውሮፕላን ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ ነበር ካቡ ኤር በተባለ ኩባንያ የተቀጠረው። በካዱና ፖሊ ቴክኒክ ለመማር አመልክቶ የትምህርት ማስረጃዎቹን በጊዜው ባለማስገባቱ ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው መሀመድ ምንም እንኳን የስራ ምርጫው ባይሆንም ለረጅም ጊዜ ያለስራ መቀመጥን ባለመምረጥ ነበር በካቡ ኤር ውስጥ ለመቀጠር የወሰነውና በአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ስራ የጀመረው።

የመሀመድ ደመወዝ እጅግ ዝቅተኛ ማለትም በቀን 200 የናይጀሪያ ናይራ ወይም 0.5 የአሜሪካን ዶላር በመሆኑ ማንም ሰው በስራው ላይ ይቆያል ብሎ አልገመተም ነበር፤ ነገር ግን ይህ ባለሩቅ ተስፋ ሀልመኛ ወጣት በስራው በመግፋት ብቻም ሳይሆን ውጤታማ ሰራተኛ በመሆን ከጊዜ ቆይታ በኋላ በሜዱግሪ ኤር በግራውንድ ስታፍነት ተቀጠረ።

ራሱን በዲሲፕሊን የታነፀና ውጤታማ ሰራተኛ ያደረገው መሀመድ በአቪየሽን ዘርፍ በርካታ እውቀቶችን እንዲያካብት አስቻለው። በቀጣይም መሀመድ በካቦ ኤር የበረራ አባልነት ላይ የማመልከት እድል አግኝቶ ስራውን መስራት ጀመረ። በዚህ ስራም ስምንት አመታትን በወር 17 ሺህ ናይራ ወይም 47 የአሜሪካን ዶላር እየተከፈለው ሰራ። ከዚህ በኋላም በበረራ ተቆጣጣሪነት ወደ ኤሮ ኮንትራክተርስ ተዛወረ።

የስራ ታታሪነቱና ፈጣን አዕምሮው በድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ትኩረትን መሳብ የቻለው መሀመድ ወርሀዊ ደመወዙ በወር ወደ 170 ሺህ ናይራ ወይም 469 የአሜሪካን ዶላር ከፍ አለ። ይህንን ማመን ያቃተው መሀመድ የመጀመሪያ የደመወዝ ክፍያ ቼኩን ሲቀበል ገንዘቡን ለመመለስ ሞክሮ እንደነበር ተገልጿል።

የሚያገኘውን ደመወዝ በዋዛ ፈዛዛ ማጥፋት ያልፈለገው መሀመድ ቁጠባ በመጀመር አብራሪ የመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ጉዳዩን ለዋና ዳይሬክተሩ አስረዳ፤ ዳይሬክተሩም የመሀመድን ሃሳብ በመደገፍ ድጋፍ ተደርጎለት በካናዳ የግል አብራሪነት ፈቃድ ለማግኘት ትምህርቱን ጀምሮ በስኬት አጠናቀቀ።

መሀመድ ወደ ናይጀሪያ ከተመለሰ በኋላ የንግድ አብራሪነት ፈቃድ መያዝ ቢፈልግም በቂ ገንዘብ ስላልነበረው ይህንን ማሳካት አልቻለም፤ ይሁን እንጂ ችግሩ ይህንን ህልሙን እና ጠንካራ መንፈሱን ሳይጎትተው ወደ ፊት በመገስገስ የድርጅቱን ም/ዋና ዳይሬክተር ድጋፍ በመጠየቅ ታማኝነቱና ስራ ወዳድነቱ በኩባንያው ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግለት ረዳው።

ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ካናዳ በመሄድ የንግድ አውሮፕላን አብራሪነት ስልጠናውን አጠናቆ ወደ ትውልድ ሀገሩ ናይጀሪያ ተመለሰ። ከ24 አመታት ጠንካራና ውጤታማ የስራ ጊዜያት በኋላ መሀመድ በአዝማን ኤር ውስጥ የአውሮፕላን አብራሪ ሆኖ በመቀጠር ህልሙን እውን አደረገ። አሁን መሀመድ በዚህ አየር መንገድ ውስጥ በአብራሪነት ስራውን እየሰራ ይገኛል፡

የሴይንት ፒተርስበርግ ፖሊስ ቦርሳቸው ውስጥ የተቆረጥ የሰው ልጅ እጅ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸውን የታሪክ ምሁር በቁጥጥር ሥር አዋለ።

ፕሮፌሰሩም ፍቅረኛቸውን እንደገደሉ አምነዋል። ጉምቱው ፕሮፌሰር ኦሌግ ሶኮሎቭ ሰክረው ወንዝ ውስጥ ወድቀው ነው የተገኙት። ወንዝ አካባቢ የተገኙትም እጁን ሊጥሉት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

ሰውዬው ከተያዙ በኋላ ቤታቸውን የፈተሸው ፖሊስ የፕሮፌሰሩ የቀድሞ ተማሪ የነበረች የ24 ዓመት ወጣት ሬሳ አግኝቷል። የፕሮፌሰሩ ቤት ውስጥ ጭንቅላቷ ተቆርጦ ሬሳዋ የተገኘችው ሴት አናስታሲያ የሺቼንኮ ከፕሮፌሰሩ ጋር በርካታ ፅሑፎች ያሳተመች ተማሪ ናት።

የናፖሌዮን ታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሶኮሎቭ በፈረንሳይ የሌጌዎን ክብር የተሰጣቸው ሰው ናቸው። የግለሰቡ ጠበቃ የሆኑ ሰው ፕፎፌሰሩ ፍቅረኛቸው የነበረችውን ወጣት መግደላቸውን አምነዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የ63 ዓመቱ ፕሮፌሰር የወጣቷን ሬሳ ካስወገዱ በኋላ እንደናፖሌዮን ለብሰው አደባባይ ላይ ራሳቸውን ሊያጠፉ አስበው እንደነበርም ታውቋል። ግለሰቡ ከፍቅረኛቸው ጋር ባለመግባባታቸው ምክንያት እንደገደሏትና ጭንቅላቷን እንደቆረጡ ለፖሊስ አምነዋል።

የፕሮፌሰሩ ጠበቃ የሆኑት ሰው ደንበኛቸው ‘ሂፖተርሚያ’ [ሰውነት ከፍተኛ የሙቀት መጠን ሲያጥረው የሚከሰት በሽታ] የተሰኘ በሽታ ተጠቂ መሆናቸውን አውስተው የጭንቀት ተጠቂ ሳይሆኑ አይቀርም ብለዋል።

የታሪክ ተመራማሪው ስለ ናፖሌዮን በርካታ መፃሕፍትን ፅፈዋል። አልፎም በርካታ ፊልሞች ላይ የታሪክ ተመራማሪ እና አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።

የፈረንሳይ ማሕበራዊ ፍትህ፣ ኢኮኖሚክስ እና ፖለቲካ ኢንስቲትዩት አባልም ነበሩ። ነገር ግን ዜናውን የሰማው ይህ የተከበረ የት/ት ተቋም ግለሰቡን ከአባልነት ሰርዟል።

ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና ለጤና ጠቃሚው የቱ ነው

ልጅቱ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣ ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ ሊያጽናናትና ሊያበረታት ሞከረ፡፡ እርሷ ግን ማማረሯን፣ መማረሯንም አላቆመቺም፡፡ እንዲያውም ምሬቷ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ፤ ኑሮዋንም እየጠላቺው፣ ፈተናዋንም እየፈራቺው መጣች፡፡

አንድ ቀን መኖር አስጠልቷት፣ ችግሩና መከራም በርትቶባት፣ ምሬቷም ጫፍ ደርሶ መጣች፡፡ ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ መኖር አልፈልግም፤ ይህንን ያህልስ እኔ ለምን እፈተናለሁ፤ ለምንስ ችግር ይበረታብኛል፤ ለምንስ ሁሉም ነገሮች ይጠሙብኛል፤ በቃ እኔ መኖር የለብኝም›› እያለች ታለቅስ ነበር፡፡አባቷ ምክሩ ሁሉ እንዳልሠራ፣ የነገራትንም ሁሉ እንደዘነጋቺው ተረዳ፡፡‹‹ተከተይኝ›› አላትና ወደ ማዕድ ቤት ገቡ፡፡

ወንበር ሰጣትና እርሱ ወደ ምግብ ማብሰያው ሄደ፡፡ ኮመዲኖውን ከፈተና ዕንቁላል፣ ድንችና የተፈጨ ቡና ይዞ መጣ፡፡ እርሷ ግን ትዕግሥቷ አልቆ ነበር፡፡ በልቧም ‹‹እኔ ኑሮ መርሮኝ እርሱ ምግብ ሊጋብዘኝ ይፈልጋል›› ትል ነበር፡፡ ‹‹አባቴ ችግሬን አልተረዳውም ማት ነው፤ ርቦኝ የተነጫነጭኩ መሰለው›› አለች፡፡ ‹‹እኔ ምግብ አልፈልግም፣ ቡናም አልጠጣም፤ በቃ እንዲያውም እሄዳለሁ›› አለችው፡፡ ዝም አላት፡፡

ሦስቱ ምድጃዎች ላይ የሻሂ ማፍያዎችን ጣደ፡፡ በአንደኛው ላይ ዕንቁላሉን፣ በሌላው ላይ ድንቹን፣ በሦስተኛውም ላይ የተፈጨውን ቡና ጨመረው፡፡ ከዚያም ወደ ልጁ መጣና ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ምን እየሠራህ ነው፤ የኔ ችግርና ምግብ ምን አገናኛቸው፤ ቤቴ ውስጥ ሞልቷልኮ፤ ሕጻን አደረግከኝ እንዴ፤ ዕድሌ ነው፣ አንተ ምን ታደርግ›› ትነጫነጫለች፣ ትቆጣለች፣ ታማርራለች፡፡ አባቷ ግን ዝም ብሎ ያዳምጣታል፡፡ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ትከሻዋን እየደባበሰ ዝም አላት፡፡ ቃል ከአፉ አልወጣም፡፡

ውኃው መንፈቅፈቅ ጀመረ፡፡ አልፎ አልፎም ውኃው ከመክደኛው ወጥቶ እሳቱ ላይ ሲንጠባጠብ ‹ትሽ› የሚለው ድምጽ ይሰማ ነበር፡፡ አባቷ ድንገት ቆመ፡፡ ደንግጣ እንደተቀመጠች አቅንታ አየቺው፡፡ ‹‹በይ ተነሺ› አላት፡፡ ዘገም ብላ ተነሣቺ፡፡

‹‹ሦስቱንም የሻሂ ማፍያዎች ክፈቻቸው›› አላት፡፡‹‹ለምን?›› አለች ግራ ተጋብታ፡፡
‹‹ግዴለም እሺ በይኚ››መንቀር መንቀር እያለቺ ወደ ማንደጃው ሄደቺ፡፡

‹‹ሦስቱም ማፍያዎች ውስጥ ያሉትን ነገሮች አውጫቸው›› አላት፡፡ ዕንቁላሉንና ድንቹን በጭልፋ አወጣቺና ሰሐኖቻቸው ላይ አደረገቻቸው፡፡ ቡናውን ስኒ ላይ ቀዳቺው፡፡

እና ምን ይሁን?›› አለቺው ልጁ፡፡‹‹ድንቹን ተጫኚው፣ ዕንቁላሉን ላጭው፣ ቡናውንም ቅመሺውተመልከቺ፤ ድንቹ ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ጠንካራ ነበረ፡፡ የፈላው ውኃ ግን ጠንካራውን ድንች ፈረካከሰው፡፡ ዕንቁላሉ የፈላው ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ውጩ ጠንካራ ውስጡ ግን ፈሳሽና ስስ ነበረ፡፡ ውኃው ሲፈላ ግን ውስጡ ፈሳሽና ስስ የነበረው አስኳሉ ጠንካራ ሆነ፡፡ ቡናው ሲፈላ ቤቱን በመዓዛው ዐወደው፣ የአካባቢውንም ጠረን ቀየረው፤ ጣዕሙም ልዩ ሆነ፡፡

‹‹ሦስቱም በተመሳሳይ ማፍያ በተመሳሳይ ዓይነት እሳት ነበር የተጣዱት፡፡ ችሀግራቸው አንድ ነው፤ ለአንድ ዓይነት ችግር የሰጡት ምላሽ ግን የተለያየ ነው፡፡ ድንቹ ጥንካሬውን አጣ፣ ዕንቁላሉ አስኳሉ ጠነከረ፣ ቡናው መዓዛውና ጣዕሙን ይበልጥ እንዲያወጣው አደረገው፡፡ ልጄ ያንቺም ችግር ያለው ከገጠመሽ ችግርና ፈተና አይደለም፡፡ ለገጠመሽ ችግርና ፈተና ከምትሰጪው ምላሽ እንጂ፡፡ የተለያዩ ሰዎች አንድ ዓይነት ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል፤ እንዲያውም በኑሮው ውስጥ የማይፈተን ሰው የለም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ለችግርና ለፈተና የሚሰጡት ምላሽ የተለያየ ነው፡፡

‹‹ፈተና አንዳንዱን እንደ ድንች ጥንካሬውን አጥቶ እንዲፈረካከስ ያደርገዋል፡፡ አንዳንዱን ሰው ደግሞ እንደ ዕንቁላሉ ውስጡን ያጠነክርለታል፤ ሞራሉን ገንብቶ፣ መንፈሱን ያበረታዋል፡፡ እሳት የብረትን ዝገት እንዲያስወግድ ፈተናም የአንዳንዱን የስንፍና ዝገት ያስወግድለታል፣ ውስጡን ጠንካራ ያደርግለታል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ችግርና መከራው፣ ፈተናና ስቃዩ ውስጣዊ መዓዛውንና ጣዕሙን እንደ ቡናው እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ ውስጣዊ ችሎታውን፣ ዕምቅ ዐቅሙን፣ የተዳፈነ ተሰጥዖውን፣ ለሌሎች ሊተርፍ የሚችል ጸጋውን ያወጣለታል፡፡

‹‹ውሳኔው በእጅሽ ላይ ነው ልጄ፤ ችግር እንዳይመጣ፣ ፈተናም እንዳይኖር፣ መከራም እንዳይገጥም ተግዳሮትም እንዳይደርስ ማድረግ አይቻልም፡፡ ራስን ወይ ድንች፣ ወይ ቡና ወይም ደግሞ ዕንቁላል ማድረግ ግን ይቻላል፡፡››

ልጁ ጉንጩን ስማው አንገቷን እየነቀነቀች ወጣች፡፡ ውስጧም ‹ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና› ይል ነበር፡፡ ሌሎችም እንዲያነብቡት ሼር ያድርጉላቸው፡፡

እውነት በአቶ አንዳርጋቸው ይሁንታ ግብፅ ተስማማች ?

በውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የኢትዮጵያ መንግስት የልዑካን ቡድን አባላት በአባይጉዳይ የመንግስትን አቋም ለአሜሪካ መንግስት ለማስረዳት ከግብፅ እና ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋር እዚህዋሽንግተን ዲስ ተጠርተው መምጣታቸው ይታወቃል::

በታጠረ ሚዲያ አሰራር አሁንም ድረስ የሚያምነው የዶር አብይ አገዛዝ ታዲያ በዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲውበኩል ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ስለአባይ ጉዳይ ለመደራደር የመጡት የመንግስት ባለስልጣናት በጋዜጠኞችበነፃነት እንዳይጠየቁ ውስን የሚዲያ ተቋማትን እና ዲጄዎችን ብቻ  መጋበዙ ብዙዎችን አስገርሟል:: ድንቄምለዉጥ እና መደመር እንዲሉ!!

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተለይተው የተጋበዙት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ለኢቲቪ የእጅአዙር ወኪል ሆና በኢምባሲው ውስጥ የምትሰራው ንጋት በቃና እና አንድ የፌስቡክ ዲጄ እንዲሁም ጥቂቶችበውስጥ የተመረጡ ብቻ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል::

በተረኛ አገዛዝ ሰዎች እንደሚዘወር የሚነገርለት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አምባሳደር ፍፁም አረጋየጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሀላፊ ሆነው በመስራታቸው ስለሚዲያ አሰራር ያውቃሉ ተብሎ ቢገመተም“ለውጡን ”አሜን ብሎ የተቀበለውን ኢሳትን እንኳ አለመጋበዛቸው አሁንም ከፍርሀት ኮፈን ያልተላቀቁ እና አቅመ ቢስ መሆናቸውን አስመስክረዋል::አይ መደመር! አይ ፍልስፍና ! “ማሞ ሌላ !መታወቂያው ሌላ ! ” አሉ የአራዳ ልጆች!!ይሰማዎታል ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር?

በጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው

የጃዋር አስገራሚ ታሪክ ከዱመና ደሳሳ ጎጆ እስከ አሜሪካ እና ቦሌ ቅንጡ ቤት

ጃዋር ማን ነው ጃዋር ከትንሿ ከተማ ዱሙጋ የተወለደው በ 1986 አ.ኤ,አ የተወለደ ጃዋር እናቱ ኦርቶዶክስ አባቱ ደግሞ ሙስሊምመሆናቸው 90% ሙስሊም በሆነባት ዱሙጋ የተለያዩ ሀይማኖት የሚከተሉ ሰዎች መጋባት ያልተለመደ ድርጊትስለነበር ጃዋር በጊዜው ልዩ አድርጎት ነበር ።

 መደበኛ ትምህርቱን በ አሰላ ጀመረ ከዛም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ናዝሬት(አዳማ) ተማረ ከዛ በኋላ ነውየራሴን ማንነት እንዳውቅ ረድቶኛል ካለው ዩንቨርስቲ  “united world college of south east Asia” ከዛም Stanford university ፖለቲካል ሳይንስ አጠና ። በዚህም ወቅት ነበር በ 2006 አ.ኤ.አ የዛሬው ጃዋር ተወለደ ወደ አክትቪዝሙተቀላቀለ በ 2006 እ.ኤ.አ ለብዙ ኦሮሞ ወጣቶች ማህበር እንደ ዣንጥላ ይሆናል ያለውን አለምአቀፋዊ የ ኦሮሞወጣቶች ማህበርን (IOYA) መሰረት ።

በጊዜውም በ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ሚፅፋቸው ፅሁፎች እና በሚናገራቸው ሀሳቦች በውጭ በሚኖረውኢትዮጵያዊ ተሰሚነቱ እየጨመረ መጣ በጊዜው የ ኦነግን (OLF) አካሄድ የ ኦሮሞ ጥቅሞችን አያስጠብቅም ብሎይተች ነበር ከነዚህ ፁሁፎች “Failure to Deliver: The Journey of the Oromo Liberation Front in the Last Two Decades” አንዱ ነበር  ።

 ጃዋር አክቲቪስት ሁኖ በመጣበት ጊዜ OLF  ያለ መሪ የቀረበት ፣ ኦሮሞም ” የተበታተነበት” ጊዜ ነበር ይህ ወቅትሀሳቡን ህዝቡ በሚረዳው መልኩ ያቀረበበት እንዲሁም ወጣቱን ለ አዲስ ትግል(ለ አዲስ የ ኦሮሞ ተቃውሞፖለቲካ) ያነሳሳበት ጊዜ ነበር ይህ ወቅት ለአሁኑ ጃዋር ወርቃማ ዘመን ነበር ።

ጃዋር በትግሉ የነበረው አስተዋጽኦ : ጃዋር የቄሮን ትግል በመምራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው ለውጡም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅአድርጓል ። ለውጡም አሁን ያለውም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለ ጃዋር መመልከት ፈፅሞ አይቻልም ። 

ጃዋር አሁን ፣ 

የ OMN ዳይሬክተር እና ከ 1.7 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ባሉት የፌስቡክ  ገፁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ቀጥተኛም ሆነበተዘዋዋሪ እየተሳተፈ ከሚገኙ ሰዎች አንዱ (ዋነኛ ) በመሆን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ይገኛል ። ነገርግን ከቅርብ ጊዜወዲህ ቄሮን እንደፈለገ መንዳት ባለመቻሉ የሱ አስተዋጽኦ እየቀነሰ ይገኛል ። አሁን ላይ የድሮ ሀይሉን ለመመለስከዚህ በፊት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ስልቶችን እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦችንና ሀይሎችን በመጨመርእየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። 

የጃዋር ባህሪ :ጃዋር በባህሪው ሀሳቡን በነፃነት መናገር የሚወድ ነው በአንድ ቃለመጠይቅ በማንነቱ ደህንነት እንደማይሰማውእና በ self confidence አለመኖሩን ከ ፖለቲካው እና ከ ኦሮሞ ማህበራት ለሁለት አመት ርቆ እንደነበር ይናገራል ። 

የጃዋር ቅንጡ ቪላ ከጃዋር መሀመድ ቅንጡ ህይወት ጀርባ ያሉ ሚስጥሮች እነሆ! የደህንነት ካሜራ የተገጠመለት 300 ካሬ እጅግዘመናዊ ቪላ ቤት በአዲስ አበባ።እያንዳንዳቸው 10 ሚለዮን ብር የሚያወጡ 3 መኪኖች!! እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ 10 ጠባቂዎች!! 5 ምግብአብሳዮች!!

በርካቶች ይህን የጃዋር ቅንጡ ህይወት ከሳውዲ ንጉስ ጋር አመሳስለውታል፡፡ጀዋር በቅርብ ቃለምልለሱ እኔም አብይም በv8 መኪና ነው የምንሄደው ማለቱ ይተወሳል፡፡

ጃዋር በአሁኑ ግዜ የጃዋር ታሪክ ለብዙዎቻችን እንደ ማነቃቂያ ነው ። እሱ በውሸት ታሪክ ተመስርቶ ይህን ያህል ለውጥ ካመጣ እኛበዕውነተኛ ማስረጃዎች እሱን ለህግ ማቅረብ አያቅተንም የሚሉ ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር ተነስተዋል ::

የዛሬ ዋና ዋና ሰበር ዜናዎች

የዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 27/2012 የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች ጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ከሥልጣን ሊለቁ እንደሆነ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ከስልጣንየሚነሱት ቦታው ለድርጅት ወይም ብሄር ውክልና ስለተፈለገ እንደሆነ ተገምቷል፡፡ አሚር በሚንስትርነትየተሾሙት ሃች አምና በሚያዚያ ወር ሲሆን፣ በሥራቸው አድናቆትን አትርፈዋል፡፡

2.በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሃሳብ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቶችን የሚከታተሉት ልዩራፖርተር በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ የልዩ ራፖርተር ዴቪድ ኬይን ጉብኝት ከኅዳር 22-29 እንደሚዘልቅቢሯቸው ባሰራጨው መረጃ ጠቁሟል፡፡ በቆይታቸው ከመንግሥት ሃላፊዎች፣ ጋዜጠኞች፣ መብት ተሟጋቾች እናሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በሀገሪቱ ስላለው ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይነጋገራሉ፡፡ ማንኛውምግለሰብ በድርጅቱ ድረ ገጽ ለሰፈሩት ጥያቄዎች እስከ ኅዳርአድራሻ መልስ እንዲሰጥም ጥሪ አድርጓል፡፡ ራፖርተሩየጉብኝታቸውን ውጤት በመጭው ሰኔ ለተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል ያቀርባሉ፡፡

3.  በዋሽንግተን ውይይት የተቀመጡት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች እስከ ጥር 6 የሕዳሴ ግድብ የቴክኒክ ውይይትን ለማጠናቀቅ እና ፍትሃዊ ስምምነት ላይ መድረስ ተስማምተናል ሲሉ መግለጫአውጥተዋል፡፡ ስምነት ካልደረሱ ግን የ2008ቱ Declaration of Principles አንቀጽ 10 ሥራ ላይእንዲውልተስማምተዋል፡፡ “ሀገራቱ በመግለጫው አተረጓጎም ወይም አተገባበር ላይ ያላቸውን ልዩነት በወይይት ወይምድርድር ይፈታሉ፤ ካልተስማሙ አደራዳሪ ሊጠይቁ ወይም ወደ መሪዎች ጉባዔ ሊመሩት ይችላሉ”- ይላል አንቀጹ፡፡በቀጣይ የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባዎች አሜሪካና ዐለም ባንክ በታዛቢነት ይገኛሉ፡፡ ሚንስትሮቹ ኅዳር 29 እና ጥር 4 ድጋሚ በዋሽንግተን ይሰበሰባሉ፡፡

4.  ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ ሰጭዎችን ምዝግባ ዛሬ ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ ምዝገባውበሲዳማ ዞን እና ሐዋሳ ከተማ በ1 ሺህ 692 ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እየተካሄደ ነው፡፡ በሀዋሳና አካባቢዋ ብቻ225 ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ምዝገባው እስከ ሕዳር 6 ይቆያል፡፡

5. ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ላኪዎች የተቀመጠላቸውን የሕግ አግባብ ብቻ እንዲከተሉ የሚያስገድድመመሪያ እንደሚያወጣ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ መንግሥት የወጭ ንግዱን ግብይት ሥርዓት ይከታተላል፡፡ ከዐለምዐቀፍ ገበያ ጋር የማይጣጣም የግበይት ሥርዓት ለወጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል ምክንያት ሆኗል፡፡ የውጭምንዛሬ ለማግኘት ሲሉ ምርታቸውን በርካሽ የሚሸጡ እና የከሰሩ አስመስለው ለመንግሥት ሪፖርትየሚያደርጉም ነጋዴዎች አሉ፡፡

6. ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሃፊነቱን ዛሬ በይፋ ከተሰናባቹ ዋና ጸሃፊ ከኬንያዊው አምባሳደር ሙሀቡብማሊም መረከባቸው ታውቋል፡፡ መረጃውን ዛሬ ከቀትር በኋላ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩት፣ የኢጋድ ከፍተኛ የሥራሃላፊ የሆኑት ኑር ሞሐመድ ሺክ ናቸው፡፡

7. የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የተቀዋሚ መሪ ሬክ ማቻር በኡጋንዳው ለዝግ ውይይትመቀመጣቸውን ዴይሊ ሞኒተር አስነብቧል፡፡ አምና በመስከረም በፈረሙት ሰላም ስምምነት መሠረት እስከ ኅዳር12 የአንድነት ሽግግር መንግሥት መመስረት አለበት፡፡ ሆኖም የጋራ ጦር ሠራዊት ምስረታ እና የክልሎች ወሰንአጨቃጫቂ ሆነዋል፡፡ የሱዳንና የኬንያ ተወካዮች በውይይቱ ይገኛሉ፤ ኢትዮጵያ ተወካይ ስለመላኳ አልታወቀም፡፡ 

ጉድ ከአዞ መንጋጋ ጏደኛዋን ታደገች የ11 አመት ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2012 የጓደኛዋን ህይወት ለመታደግ ከአዞ ጋር ትንቅንቅ ያደርገችው ርብቃ የተባለች የ11 ዓመትዋ ታዳጊ ብዙዎቹን እያነጋገረች ነው ፡፡ ርብቃ እና ጓደኟዋ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ ወንዝ ዋኝተው ሲመለሱ÷ ከውሃ ውስጥ ጩኸት ይሰማሉ፡፡

የ11 ዓመቷ ርብቃም ጩኸቱ ወዳለበት ስትመለከት የ9ኝ ዓመቷ ጓደኛዋ ላቶያ ሙዋኒ በአዞ እየተጎተተኝ መሆኑን ተመለከተች፡፡በሁኔታው  ከፍተኛ ድንጋጤ የተሰማት ርብቃ ጓደኛዋን ለመታደግ ወደ ውሃው ዘላ ገብታለች፡፡

በአካባቢው አብረዋቸው ከነበሩት ጓደኞቻቸው የተወሰኑት  በድንጋጤ ባሉበት ሲቆሙ የተወሰኑት ደግሞ ከአካባቢው ተሰውረዋል፤ ያን ማድረግ ያልቻለችው ርብቃ ወደ ውሃው በመግባት ከአዞው ጋር ትንቅንቅ አድርጋለች፡፡

ወደ ወንዙ ዘላ የገባቸው ርብቃ የዓዞ ጭንቅላት ላይ በመውጣት በባዷ እጇ ስትመታው እደነበረ በመግለፅ በጣቶቿ የአዞው ዓይን  ላይ ጥቃት ስትፈፅም አዞ ጓደኟን እንደለቀቃት ተናግራለች፡፡

አዞው ጓደኛዋን ከለቀቃት በኋላ ጉዳት ለማድረስ  እንዳልሞከረ የተናገረችው ርብቃ በዋና ጓደኞቻቸው ወደ ሚገኙበት ስፋራ ማቅናታቸውን ገልፃለች፡፡ምንጭ ኦዲቲ ሴንተራል ሼር ያድርጉት

የስልክ ቻርጅ እያለቀብዎት ተቸግረዋል

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮችአንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡

ታዲያ፣ በዚህ ዙሪያ ለሳይቴክ ደንበኞች መላ የሚሆን ነገር አናቀርብላቸውም ብለን አሰብን… ምን ትላላችሁ?ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡

የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች

1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀምትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡

2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀምሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡

3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደርበምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡

ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡

4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋትሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡

5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅየማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡