ከፅዳት ሠራተኝነት እስከ አብራሪነት

ከወደ ናይጄሪያ የተሰማ የአንድ ስኬ ታማ ግለሰብን ታሪክ ልናስነብባችሁ ወደናል። ኢንተለጀንስ ዶት ኮም እንዳስነበበው ግለሰቡ አብራሪ የመሆን ህልሙን የጀመረው ከአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ተነስቶ ሲሆን አሁን ላይ የንግድ አውሮፕላን አብራሪ ለመሆን በቅቷል። የዚህ ስኬታማ ሰው አጭር የስኬት ታሪክ እንደሚከተለው ነው።

ናይጀሪያዊው መሀመድ አቡበከር ከዛሬ 24 አመታት በፊት የአውሮፕላን ፅዳት ሰራተኛ ሆኖ ነበር ካቡ ኤር በተባለ ኩባንያ የተቀጠረው። በካዱና ፖሊ ቴክኒክ ለመማር አመልክቶ የትምህርት ማስረጃዎቹን በጊዜው ባለማስገባቱ ተቀባይነት ሳያገኝ የቀረው መሀመድ ምንም እንኳን የስራ ምርጫው ባይሆንም ለረጅም ጊዜ ያለስራ መቀመጥን ባለመምረጥ ነበር በካቡ ኤር ውስጥ ለመቀጠር የወሰነውና በአውሮፕላን የፅዳት ሰራተኝነት ስራ የጀመረው።

የመሀመድ ደመወዝ እጅግ ዝቅተኛ ማለትም በቀን 200 የናይጀሪያ ናይራ ወይም 0.5 የአሜሪካን ዶላር በመሆኑ ማንም ሰው በስራው ላይ ይቆያል ብሎ አልገመተም ነበር፤ ነገር ግን ይህ ባለሩቅ ተስፋ ሀልመኛ ወጣት በስራው በመግፋት ብቻም ሳይሆን ውጤታማ ሰራተኛ በመሆን ከጊዜ ቆይታ በኋላ በሜዱግሪ ኤር በግራውንድ ስታፍነት ተቀጠረ።

ራሱን በዲሲፕሊን የታነፀና ውጤታማ ሰራተኛ ያደረገው መሀመድ በአቪየሽን ዘርፍ በርካታ እውቀቶችን እንዲያካብት አስቻለው። በቀጣይም መሀመድ በካቦ ኤር የበረራ አባልነት ላይ የማመልከት እድል አግኝቶ ስራውን መስራት ጀመረ። በዚህ ስራም ስምንት አመታትን በወር 17 ሺህ ናይራ ወይም 47 የአሜሪካን ዶላር እየተከፈለው ሰራ። ከዚህ በኋላም በበረራ ተቆጣጣሪነት ወደ ኤሮ ኮንትራክተርስ ተዛወረ።

የስራ ታታሪነቱና ፈጣን አዕምሮው በድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ትኩረትን መሳብ የቻለው መሀመድ ወርሀዊ ደመወዙ በወር ወደ 170 ሺህ ናይራ ወይም 469 የአሜሪካን ዶላር ከፍ አለ። ይህንን ማመን ያቃተው መሀመድ የመጀመሪያ የደመወዝ ክፍያ ቼኩን ሲቀበል ገንዘቡን ለመመለስ ሞክሮ እንደነበር ተገልጿል።

የሚያገኘውን ደመወዝ በዋዛ ፈዛዛ ማጥፋት ያልፈለገው መሀመድ ቁጠባ በመጀመር አብራሪ የመሆን ህልሙን እውን ለማድረግ ጉዳዩን ለዋና ዳይሬክተሩ አስረዳ፤ ዳይሬክተሩም የመሀመድን ሃሳብ በመደገፍ ድጋፍ ተደርጎለት በካናዳ የግል አብራሪነት ፈቃድ ለማግኘት ትምህርቱን ጀምሮ በስኬት አጠናቀቀ።

መሀመድ ወደ ናይጀሪያ ከተመለሰ በኋላ የንግድ አብራሪነት ፈቃድ መያዝ ቢፈልግም በቂ ገንዘብ ስላልነበረው ይህንን ማሳካት አልቻለም፤ ይሁን እንጂ ችግሩ ይህንን ህልሙን እና ጠንካራ መንፈሱን ሳይጎትተው ወደ ፊት በመገስገስ የድርጅቱን ም/ዋና ዳይሬክተር ድጋፍ በመጠየቅ ታማኝነቱና ስራ ወዳድነቱ በኩባንያው ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግለት ረዳው።

ለሁለተኛ ጊዜ ወደ ካናዳ በመሄድ የንግድ አውሮፕላን አብራሪነት ስልጠናውን አጠናቆ ወደ ትውልድ ሀገሩ ናይጀሪያ ተመለሰ። ከ24 አመታት ጠንካራና ውጤታማ የስራ ጊዜያት በኋላ መሀመድ በአዝማን ኤር ውስጥ የአውሮፕላን አብራሪ ሆኖ በመቀጠር ህልሙን እውን አደረገ። አሁን መሀመድ በዚህ አየር መንገድ ውስጥ በአብራሪነት ስራውን እየሰራ ይገኛል፡

የሴይንት ፒተርስበርግ ፖሊስ ቦርሳቸው ውስጥ የተቆረጥ የሰው ልጅ እጅ አግኝቼባቸዋለሁ ያላቸውን የታሪክ ምሁር በቁጥጥር ሥር አዋለ።

ፕሮፌሰሩም ፍቅረኛቸውን እንደገደሉ አምነዋል። ጉምቱው ፕሮፌሰር ኦሌግ ሶኮሎቭ ሰክረው ወንዝ ውስጥ ወድቀው ነው የተገኙት። ወንዝ አካባቢ የተገኙትም እጁን ሊጥሉት ሳይሆን አይቀርም ተብሏል።

ሰውዬው ከተያዙ በኋላ ቤታቸውን የፈተሸው ፖሊስ የፕሮፌሰሩ የቀድሞ ተማሪ የነበረች የ24 ዓመት ወጣት ሬሳ አግኝቷል። የፕሮፌሰሩ ቤት ውስጥ ጭንቅላቷ ተቆርጦ ሬሳዋ የተገኘችው ሴት አናስታሲያ የሺቼንኮ ከፕሮፌሰሩ ጋር በርካታ ፅሑፎች ያሳተመች ተማሪ ናት።

የናፖሌዮን ታሪክ ተመራማሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ሶኮሎቭ በፈረንሳይ የሌጌዎን ክብር የተሰጣቸው ሰው ናቸው። የግለሰቡ ጠበቃ የሆኑ ሰው ፕፎፌሰሩ ፍቅረኛቸው የነበረችውን ወጣት መግደላቸውን አምነዋል ሲሉ ተናግረዋል።

የ63 ዓመቱ ፕሮፌሰር የወጣቷን ሬሳ ካስወገዱ በኋላ እንደናፖሌዮን ለብሰው አደባባይ ላይ ራሳቸውን ሊያጠፉ አስበው እንደነበርም ታውቋል። ግለሰቡ ከፍቅረኛቸው ጋር ባለመግባባታቸው ምክንያት እንደገደሏትና ጭንቅላቷን እንደቆረጡ ለፖሊስ አምነዋል።

የፕሮፌሰሩ ጠበቃ የሆኑት ሰው ደንበኛቸው ‘ሂፖተርሚያ’ [ሰውነት ከፍተኛ የሙቀት መጠን ሲያጥረው የሚከሰት በሽታ] የተሰኘ በሽታ ተጠቂ መሆናቸውን አውስተው የጭንቀት ተጠቂ ሳይሆኑ አይቀርም ብለዋል።

የታሪክ ተመራማሪው ስለ ናፖሌዮን በርካታ መፃሕፍትን ፅፈዋል። አልፎም በርካታ ፊልሞች ላይ የታሪክ ተመራማሪ እና አማካሪ ሆነው አገልግለዋል።

የፈረንሳይ ማሕበራዊ ፍትህ፣ ኢኮኖሚክስ እና ፖለቲካ ኢንስቲትዩት አባልም ነበሩ። ነገር ግን ዜናውን የሰማው ይህ የተከበረ የት/ት ተቋም ግለሰቡን ከአባልነት ሰርዟል።

ጉድ ከአዞ መንጋጋ ጏደኛዋን ታደገች የ11 አመት ታዳጊ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 25፣ 2012 የጓደኛዋን ህይወት ለመታደግ ከአዞ ጋር ትንቅንቅ ያደርገችው ርብቃ የተባለች የ11 ዓመትዋ ታዳጊ ብዙዎቹን እያነጋገረች ነው ፡፡ ርብቃ እና ጓደኟዋ በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ ከሚገኝ ወንዝ ዋኝተው ሲመለሱ÷ ከውሃ ውስጥ ጩኸት ይሰማሉ፡፡

የ11 ዓመቷ ርብቃም ጩኸቱ ወዳለበት ስትመለከት የ9ኝ ዓመቷ ጓደኛዋ ላቶያ ሙዋኒ በአዞ እየተጎተተኝ መሆኑን ተመለከተች፡፡በሁኔታው  ከፍተኛ ድንጋጤ የተሰማት ርብቃ ጓደኛዋን ለመታደግ ወደ ውሃው ዘላ ገብታለች፡፡

በአካባቢው አብረዋቸው ከነበሩት ጓደኞቻቸው የተወሰኑት  በድንጋጤ ባሉበት ሲቆሙ የተወሰኑት ደግሞ ከአካባቢው ተሰውረዋል፤ ያን ማድረግ ያልቻለችው ርብቃ ወደ ውሃው በመግባት ከአዞው ጋር ትንቅንቅ አድርጋለች፡፡

ወደ ወንዙ ዘላ የገባቸው ርብቃ የዓዞ ጭንቅላት ላይ በመውጣት በባዷ እጇ ስትመታው እደነበረ በመግለፅ በጣቶቿ የአዞው ዓይን  ላይ ጥቃት ስትፈፅም አዞ ጓደኟን እንደለቀቃት ተናግራለች፡፡

አዞው ጓደኛዋን ከለቀቃት በኋላ ጉዳት ለማድረስ  እንዳልሞከረ የተናገረችው ርብቃ በዋና ጓደኞቻቸው ወደ ሚገኙበት ስፋራ ማቅናታቸውን ገልፃለች፡፡ምንጭ ኦዲቲ ሴንተራል ሼር ያድርጉት

የስልክ ቻርጅ እያለቀብዎት ተቸግረዋል

የሞባይል ባትሪንእድሜ ለመጨመር 5 ቁምነገሮችአንዳንድ ጊዜ ከበሽታ ባልተናነሰ በእለት ተእለት ኑሯችን ጤና የሚነሱን አይነት ችግሮች ይገጥሙናል፡፡ ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን የእለት ተዕለት ህይወታችን ውስጥ የሚጎረብጡ ጉዳዮች ይገጥሙናል፡፡ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አብዛኛዎቻችንን ከሚጎረብጡ ጉዳዮች መካከል አንዱ የሞባይል ባትሪ ጉዳይ ነው፡፡

ታዲያ፣ በዚህ ዙሪያ ለሳይቴክ ደንበኞች መላ የሚሆን ነገር አናቀርብላቸውም ብለን አሰብን… ምን ትላላችሁ?ብዙዎቻችን የምንጠቀምባቸው ሞባይል ስልኮች የሚጠቀሙት ባትሪ የተሰሩት ከሊትየም-አይኦን (lithium-ion) ሲሆን ይሄም ባትሪ በአግባቡ ካለመጠቀም መስጠት ከሚችለው አገልግሎት ባነሰ ሁኔታ በቶሎ ይደክማል፤ ያረጃል፡፡ ይሄም ማለት ባትሪው ቻርጅ ተደርጎ በሰዓታት ውስጥ በማለቅ ተጠቃሚውን ያስቸግራል፡፡

የሞባይል ባትሪዎች ሲሰሩ ተጠቃሚው በአግባቡ ከተጠቀመበት ከ3 እስከ 5 አመት እንዲያገለግሉ ተደርገው ሲሆን ከዚህ ከተቀመጠላቸው ጊዜ ባነሰ ሁኔታ የሚያስግሩባቸውን ምክንያች እና ባትሪን በተሻለ መጠቀም የሚቻልባቸውን ዘዴዎች እንደሚከተለው እንጠቁማችኋለን፡፡የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች

1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀምትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡

2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀምሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡

3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደርበምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡

ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡

4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋትሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡

5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅየማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡

ስበር ዜና ደራርቱ በድጋሚ ቦታውን ተረከበች

አትሌት ደራርቱ ቱሉ ወደ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አባልነቷ ተመለሰችአዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 26 2012 አትሌት ደራርቱ ቱሉ ወደ ኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ስራ አስፈጻሚ አባልነቷ ተመለሰች፡፡

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤውን ጥቅምት 26 ቀን 2012 ዓ.ም በአምባሳደር ሆቴል አካሂዷል፡፡

አትሌት ደራርቱ ቱሉ በ44ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ያነሳሳቸው ቅሬታዎች ላይ ውይይት መደረጉ እና በቀጣይም በተነሱት እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ የተቋሙን ህገ ደንብ መሰረት ባደረገ መልኩ በውይይት እና በቅርበት ለመስራት ከስስምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ይህንንም ተከትሎ አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሀገሯንና ህዝቧን ለማገልገል ወደ ስራ አስፈጻሚ አባልነቷ መመለሷን ማስታወቋን የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

በዚህ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አባላቱ የተቋሙ መቋቋሚያና መተዳደሪያ ደንብን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ የተወያዩና ተጨማሪ ግብዓት የሰጡ ሲሆን በይበልጥ ረቂቅ ደንቡን ለማብሰልና ለማጽደቅ ለሌላ ጊዜ ለመገኛኘት ወስነዋል፡፡

በዚህ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ አባላቱ የተቋሙ መቋቋሚያና መተዳደሪያ ደንብን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን በይበልጥ ረቂቅ ደንቡን ለማብሰልና ለማጽደቅ ለሌላ ጊዜ ለመገኛኘት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

ፓስፖርት ለማውጣት በግልፅ የሚጠየቀው ግቦ ወይም ሙስና ህዝቡን አማርዋል

ጥቅምት 25/2012 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ፓስፖርት በማውጣት ሂደት እየተስተዋለ የመጣው ሙስና እና ብልሹ አሰራር መፈትሄ እንዲበጅለት አሳሰበ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲን የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ አፈፃፀሙን በሚመለከት ለቋሚ ኮሚቴው አቅርቧል።

በሪፖርቱ እንዳመለከተውም የፓስፖርት ክምችት ውስን በመሆኑ በአሰጣጥ ሂደቱ ችግሮች መስተዋላቸውን አመላክቷል።ከፓስፖርት እጥረት ጋር ተያይዞ ችግሩ የተወሳሰበ መሆኑም ተገልጿል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዜግነት መብት የሆነውን ፓስፖርት ለማውጣት ለወራት በቀጠሮ የሚጉላሉ እያሉ ጥቂቶች በአቋራጭ ሲወስዱ ይስተዋላል።ይህ አሰራር የኅብረተሰቡን እሮሮ እያባባሰ መጥቶ በመንግስት ላይም ጫና ማሳደሩ አልቀረም።

የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ እንዳሉት፤ በፓስፖርት አሰጣጥ ሂደት ላይ ሙስናና ብልሹ አሰራር በግልጽ ይታያል።

በመሆኑም ኤጀንሲው በፓስፖረት አሰጣጥና የቁጥጥር ጣቢያዎች ላይ የሚታየውን የተበላሸ አሰራር እንዲቆም ማደረግ አለበት ብለዋል።

በጨረታ ሂደት የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ከፓስፖርት አቅራቢው ድርጅት ጋር ያለው ግንኙነትም ሊፈተሽ ይገባል ብለዋል።

የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙጂብ ጀማል፤ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ዲዛይን በአቅራቢ ድርጅቱ እጅ መሆኑን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ ላለፉት 15 ዓመታት ኦቨር ቱር ከተባለ የፈረንሳይ ፓስፖርት አቅራቢ ድርጅት ጋር ለረጅም ዘመናት ስትሰራ መቆየቷን ጠቁመዋል።

የፈረንሳዩ ፓስፖርት አቅራቢ ድርጅት በብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ጋር በገባው ውል መሰረት የሚጠበቅበትን የፓስፖርት ቁጥር ሲያቀርብ ቆይቷል።

ሆኖም አቅራቢ ድርጅቱ በ2009 እና 2010 ዓ.ም ያቀረበው የፓስፖርት መጠን ከሚጠበቅበት በታች መሆኑ ታውቋል።

በዚህ ላይ እያለ “ኦቨር ቱር” የተባለው ድርጅት የፓስፖርት ህትመት ቴክኖሎጂውን “ኢንዴሚያ” ለተባለ ሌላ ድርጅት በመሸጡና የፓስፖርቱ ዲዛይን በድርጅቱ እጅ በመሆኑ “ኢንዴሚያ” እንዲያቀርብ ተደርጓል ብለዋል።

በ2011 ዓ.ም የነበረው ፓስፖርት ከ200 ሺህ በታች ነበር ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የቀረበውን ፓስፖርት በጣም ለሚያስፈልጋቸው አካላት ለመስጠት ተገደናል ብለዋል።

እንደ አቶ ሙጂብ ገለፃ አንዳንዶች ፓስፖርት ለማግኘት ሲሉ በአንድ በኩል የሃሰት ማስረጃ በሌላ በኩል ደግሞ በገንዘብ እየደለሉ ለማውጣት ይጥራሉ።

የፓስፖርት የጨረታ ሂደት ዓለም አቀፍ ሂደትን የተከተለ መሆን ስላለበትና አዲስ ዲዛይን ለማውጣት ጊዜ ይወስዳል ብለዋል።

ከዚህም ባለፈ ወደ ጨረታ ከመገባቱ በፊት አሁን ከሚያቀርበው ድርጅት ጋር መልካም ግንኙነት ፈጥረን ያለንን የፓስፖርት ክምችት መጠን ማብዛት ይጠበቅብናል ነው ያሉት።

ኤጀንሲው አሁን ያለው የፓስፖርት መጠን ውስን መሆኑን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ፤ ከድርጅቱ ጋር በመነጋገር እስከ መጭው ታህሳስ ወር 400 ሺህ ተጨማሪ ፓርፖርት እናስገባለን ብለዋል።

የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዳባ፤ መልካም የሚሰሩትን በማበረታታትና አጥፊዎችን በመቅጣት ሙስናና ብልሹ አሰራር መከላከል አለበት ብለዋል።

በሁሉም የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤቶች ፓስፖርት ለማውጣት የሚታየውን ሰልፍ ለመቀነስ ሌሎች አማራጮችን እናያለን ብለዋል አቶ ሙጂብ።

አዲስ ግኝት ገላዎትን የሚታጠቡት በሙቅ ነው ወይስ በቀዝቃዛ

ስለ ቀዝቃዛ ሻወር ጥቅም ከመዳሰሳችን በፊት አንድ ቀላል እውነታ እናስቀምጥ ሙቅ ሻወር መሠረታዊ ፍላጐትሳይሆን ለመዝናኛነት እና ቅንጦት የምንጠቀምበት ነው፡፡ በአብዛኛው የሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ በቅርብበሚያገኙት ውሃ ውስጥ ሻወር ይወስዳሉ፡፡ በሃይቅ ውስጥ ዋኝተው የሚያውቁ ከሆነ በቀላሉ ሊያስታውሱየሚችሉት ነገር የውሃውን ቅዝቃዜ ነው፡፡

ግሪኮች በአንደኛው ክፍለ ዘመን ለህዝብ አገልግሎት የሚውል የሙቅ ሻወር አገልግሎትን ፈጠሩ ነገር ግንበሚገርም ሁኔታ አብዛኛዎቹ ግሪካዊያን ካለው የጤና ጥቅም አንፃር ቀዝቃዛ ሻወርን ነበር የመረጡት፡፡ታምራዊጥቅሞቹ እነሆ

1. ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በኋላ ቶሎ እንድናገግም ያረዳል! አትሌቶች ከባድ ልምምድ ካደረጉ በኋላየሚያጋትማቸውን ድካምና ህመም ለመቀነስ በበረዶ ውሃ ሻወር ይወስዳሉ/ይዘፈዘፋሉ እኛ ግን ያን ያህል እርቀትመጓዝ አይጠበቅብንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ጥቅም ለማግኝት ከልምምድ በኋላ ቀዝቃዛ ሻወር መውሰድ ተገቢነው፡፡

2. ስብን (ፋት) ለማቅለጥ! ሁለት የስብ አይነቶች በሰውነታችን ውስጥ ይገኛሉ ነጭ ስብ እና ቡናማ ስብ። ነጩንስብ እንደ መጥፎ ሰው እንቁጠረው ቡናማውን ደግሞ እንደ ጥሩ ሰው፡፡

ነጩ ስብ ሁላችንም የምናውቀው የሰውነታችን ስብ ሲሆን ሁላችንም ለማጥፋት የምታገለው ነው፡፡ሰውነታችን ከሚፈልገው በላይ የሆነ ከፍተኛ ካሎሪ

በምንወስድበት ጊዜ በሃይል(Energy) መልክ እንዲጠፋ ማድረግ ይሳነናል/ ያቅተናል በሃይል/ጉልበት መልክካልተወገደ/ካልጠፋ ግን ይህ ነጭ ስብ በታችኛው ጀርባችን፣ አንገት፣ ከዳሌ ከፍ ብሎ ባለው የመካከለኛውሰውነት ክፍል እና ከጉልበታችን ከፍ ብሎ ባለው የእግር ክፍል ላይ ይከማቻል፡፡ቡናማ ስብ ጥሩ ሰው ሲሆንየሚሰጠን ጥቅም ለሰውነታችን ሙቀት መፍጠር ነው፡፡

በከባድ ቅዝቃዜ ወቅት እነዚህ ቡናማ ስቦች ይነሳሱና ካሎሪን በማቅለጥ የሰውነታችን ሙቀት እንዲጨምርያደርጋሉ ይህም የሰውነት ክብደትን በመቀነስ ይረጋናል፡፡

3. የደም ዝውውርና በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል! ስብን ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር እንዴትእንደሚረዳን ከላይ ተመልክተናል ሰውነታችን ስብን ለማቃጠል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የበሽታ መከላከያስርዓታችንን ያነሳሳል ይህም ቫይረስን የሚዋጉነጭ የደም ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋቸዋል የእነዚህ ሴሎችመመረት በህመም የመጠቃት እድላችን

እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡ ቀዝቃዛ ሻወር አጠቃላይ የደም ዝውውርን ይጨምራል ይህም የደም ቧንቧዎችእንዳይጠነክሩ እና የደም ግፊት ያስወግዳል፡፡

4. የሚስብ ፀጉር እና ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል!በሰውነታችን ላይ ያለውን ብጉር ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር ከፍተኛ ድርሻ አለው። ሙቅ ውሃ ቆዳን ያደርቃልቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክልና ቀዳዳዎችን በመዝጋት በቆሻሻ ከመደፈን ይከላከላል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ የሚያንፀባርቅናበጣም የሚስብ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክሎችን በመዝጋት ቆሻሻ በራስ ቅላችንላይ እንዳይከማች ይረዳል፡፡

5. ደስተኛ እና ፈጣን እንድንሆን ያደርጋል!ጠዋት ከአልጋ ላይ ሲወርዱ ደብርዎትና ተጫጭኖዎት የሚይነሳማነው? ይህ ሁሉም ሰው የሚያጋጥመው ነገር ይመስለኛል ነገር ግን ጠዋት ወደ ስራ ከመሄድዎ በፊት ገናከአልጋዎ እንደወረዱ ቀዝቃዛ ሻወር ይውሰዱ፡፡

ቀዘቃዛ ውሃ በሰውነትዎ ላይ በሚፈስበት ጊዜ ለቅዝቃዜው ምላሽ በጥልቀት ይተነፍሳሉ(ይህሰውነትዎ ኦክስጂን አወሳሰዳችን በመጨመር ሰውነታችን ራሱን ለማሞቅ የሚያደርገው ሙከራ ነው፡፡የልብምትዎ ይጨምራል የዚህ ውጤት ደም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን እንዲዳረስ በማድረግ ጉልበት እንዲኖረንያደርጋል፡፡

ሳናውቅ በየቀኑ የምናደርጋቸው አንጎልን የሚጎዱ ነገሮች

ክቡራን አንባቢዎቼ ለአንጎል ጎጂ የሆኑ 8 ልማዶች በየቀኑ የምናደርጋቸው ነገርግን የማናስተውላቸው ወሳኝነጥቦች ናቸው ሼር አድርጉት1. ቁርስ አለመመገብ ቁርስ የማይመገቡ ከሆነ በሰውነትዎ ውስጥ የሚገኘውን የደም ስኳር መጠን ስለሚቀንስለአንጎል የሚደርሰውን የምግብ መጠን በማስተጓጎል ለጉዳት ይዳርገናል።

2. በህመም ወቅት በቂ እረፍት አለማድረግሰውነታችን በህመም ሲጠቃ በቂ እረፍት ማድረግ እና ከህመሙ ማገገም በአንጎል ላይ ተጨማሪ ጫና እንዳይኖርይረዳል።

3. ሲጋራ ማጤስ ሲጋራ ማጤስ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ እንደሆነ የሚታወቅ ነው። የልብ ህመም፣ የሳምባካንሰር እና ስትሮክን ከማስከተል ባለፈ በአንጎል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

4. ከፍተኛ የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች ማዘውተር ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጣፋጭነት ያላቸውምግቦችና መጠጦች ማዘውተር ለአንጎል ጉዳት መንስኤ ናቸው።

5. የአየር ብክለት አንጎል ከየትኛውም የሰውነት ክፍሎቻችን በበለጠ ኦክስጂን ያስፈልገዋል። የምንተነፍሰውአየር የተበከለ ከሆነና ለአንጎል የሚደርሰው የኦክስጅን መጠን ከቀነሰ ጉዳት ያስከትላል።

6. የእንቅልፍ እጦት እንቅልፍ አንጎልን እረፍት እንዲያገኝ የምናደርግበት ሂደት ስለሆነ በቂ እንቅልፍአለመውሰድ ለጉዳት ይዳርጋል።ለረጅም ጊዜ እንቅልፍ ማጣት የአንጎል ህዋሳት ሞትን ያፋጥናል፡፡

7. የአልኮል መጠጥ ማብዛት በቀን የምንወስደው የአልኮል መጠጥ ከፍተኛ ከሆነ የአንጎል ህዋሶቻችንን ቀስበቀስ ሊገድል ስለሚችል ከፍተኛ ጉዳት ያስከትላል።

8. የምግብ አይነቶችን አለመምረጥ ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መመገብ ለአንጎል ጤናማነት ወሳኝ ነው።ለሌሎችም ሼር ሼር ማድረግዎን አይርሱከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን ::