“ለማ መገርሳን የቀነሰ መደመር፣ መደመር አይሆንም” ዶ/ር ሔኖክ ገቢሳ

ሬዲዮው አክሎም አቶ ታዬ፣ “አቶ ለማ በኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዲፒ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ውህደቱ አስፈላጊ እንደሆነና የመደመር ዕሳቤ ከኢትዮጵያ ዐልፎ ለምሥራቅ አፍሪካም ጠቃሚ ሃሳብ እንደሆነ ተስማምተው ነው ያጸደቁት፤ የልዩነት ሃሳብ አልሰማንም። ከዚያም አልፎ በኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴና ጉባኤ፣ በኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባዎች ላይ ሁሉ የተለየ አቋም አላንጸባረቁም። በዚህ መሄድ አለብን የሚል የተለየ አማራጭ ሃሳብም አላቀረቡም” ማለታቸውን አስታውቋል።

ይህንን የአቶ ለማ አቋም አስመልክተን ያነጋገርናቸው በዋሺንግተንና ሊ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር የሆኑት ሔኖክ ገቢሳ (ዶ/ር) ውህደት ብለን የምንናገር ከሆነ ለዚች አገር ከፍተኛ ውለታ ዋሉ እንደ አቶ ለማ መገርሳ ያሉትን ሰዎች እየቀነስን ውህደቱን እውን ማድረግ አስቸጋሪ ነው ብለውናል።

ዶ/ር ሔኖክ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ በአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር ውስጥ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ሰዎችን፣ ሀሳባቸውንና እምነታቸውን ሳያካትቱ ውህደቱን ማካሄድ ከባድ ይሆናል።

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ፕሮፌሰር መረራ፣ ዶ/ር አቢይ ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ‘ለዐቢይ ትልቁ ተግዳሮት የሚሆነው የኢትዮጵያ ሕዝቦችን መርቶ ማሻገር ሳይሆን ኢህአዴግን እንደ ኢህአዴግ መርቶ መሻገር መቻልና አለመቻል ላይ ይመሰረታል’ ማለታቸውን በማስታወስ፣ በአሁኑ ሰዓትም በግንባሩ ውስጥ ያሉ ፓርቲዎች መጠላለፍ ለጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ትልቁ ተግዳሮት ሆኖበታል ብለው እንደሚያምኑ ይገልጻሉ።

“ከዚህም የተነሳ እንደሚፈለገው አብሮ ወደፊት መሄድ አልቻሉም” በማለት የእርሳቸው ፓርቲ ኢህአዴግ ተዋሀደም አልተዋሀደም የሚጠብቅበት ነገር እንዳለ አጽንኦት ሰጥተው ያስረዳሉ።

በውህደቱ ላይ አቶ ለማ እንደማይስማሙ በተባራሪ ወሬ ሲሰሙ መቆየታቸውን የሚናገሩት ዶ/ር ሔኖክ ደግሞ፤ እንዲህ ዓይነት መከፋፈል በአሁኑ ሰዓት መፈጠር አልነበረበትም ብለው እንደሚያምኑ ያስረዳሉ።

ለዚህም ምክንያት ነው ያሉትን ሲጠቅሱም፤ “በእነርሱ መካከል በሚፈጠር አለመግባባት የኦሮሞ ትግል መከፋፈል የለበትም ብዬ ስለማምን ነው” ብለዋል።

“አቶ ለማም ሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ትልቅ ውለታ የዋሉ ሰዎች ስለሆኑ ሃሳባቸውን ወደ አንድ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል” በማለትም፤ “የኦሮሞን ሕዝብ ጥያቄ እንመልሳለን ብለው ካመኑ፤ የኦሮሞ ሕዝብ መሪዎች ነን ብለው ካሉ፤ መደማመጥ አስፈላጊ ነው” ሲሉ መነጋገር አስፈላጊ መሆኑን ያሰምሩበታል።

የኢትዮጵያ መሪዎች ዲሞክራሲን አንገነባለን ሲሉ ተቃራኒ ሀሳቦችንም ማስታገድ አለባቸው ብዬ አምናለሁ የሚሉት ዶ/ር ሔኖክ፤ አሁንም ያለመግባባት መንስዔ የሆነው የውህደት ውሳኔ እንደገና መታየት አለበት ብለው እንደሚያምኑ ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የእስራኤል የልብ ህክምና ባለሙያዎች በኢትዮጵያ ህክምና ሊሰጡ ነው

መቀመጫውን እስራኤል ያደረገው ‘ሴቭ ኤ ቻይልድ’ስ ኸርት የተባለና ለትርፍ ያልተቋቋመው አለም አቀፍ የልብ ህክምና ቡድን ነገ በኢትዮጵያ የልብ ህከምና ማዕከል አገልግሎቱን ይሰጣል።ቡድኑ ለ30 ህፃናት የልብ ቀዶ ህክምና እና ሌሎች ተያያዥ ህክምናዎችን እንደሚሰጥ ፒአር ኒውስ ከዋሽንግተን ዘግቧል።

‘የህፃናትን ልብ ማዳን’ የሚል ተልዕኮ ያነገበው ቡድን በኢትዮጵያ የልብ ማዕከል ከሚሰሩትና የቡድኑ አጋር ከሆኑት ዶክተር ያየህይራድ መኮንን ጋር በመሆን በማዕከሉ ህክምናውን ይሰጣል ተብሏል።የቡድኑ አባላት በቆይታቸው ለህፃናት ቅድመ ምርመራ የሚያደርጉ ሲሆን ከዚህ በፊት ህክምና ያገኙ ክትትል ይደረግላቸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ በኢትዮጵያ ስራ የጀመረበትን 25 አመት ባለፉት ዓመታት በቡድኑ ህክምና ያገኙ 700 ኢትዮጵያውያን ህፃናት በተገኙበት ይከበራል።

ቡድኑ በመላው አለም ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖትና ዜግነት ሳይለይ የህፃናትን ልብ ለማከም ይሰራል” ሲሉ የተቋሙ ዋና ተጠሪ ሲሞን ፊሸር ተናግረዋል።

“በኢትዮጵያ የምናከናውነው ተልዕኮ ዘመኑ የሚጠይቃቸውን የልብ ህክምና ቁሳቁስ ከማሟላት አንስቶ፣ ላቦራቶሪ፣ ዘመናዊ የቀዶ ጥገና ክፍል እና የጽኑ ህክምና ክትትል ለማድረግ የሚያግዙ ባለሙያዎችንና ቁሳቁሶችን ማቅረብን ይጨምራል” ብለዋል።

በዚህም አገልግሎቱን የሚፈልጉ ህፃናትን ተደራሽ ማድረግ እንደሚቻል ገልጸው፤ ”በኢትዮጵያ የምናከናውነው ተልዕኮ የብዙ ልጆችን ህይወት የለወጠ ሲሆን በቡድናችንና በአጋሮቻችን ተግባር በእጅጉ እንደሰታለን” ብለዋል።

‘ሴቭ ኤ ቻይልድ’ስ ኸርት’ በኢትዮጵያ ዘጠኝ የልብ ህክምና ስፔሻሊስቶችን አሰልጥኗል። ዘጠኙም ባለሙያዎቹ አሁን ላይ በአገራቸው ህክምናውን እየሰጡ እንደሚገኙም ተገልጿል።ተቋሙ ከተቋቋመበት አ.አ.አ 1995 አንስቶ በ62 አገሮች ለሚገኙ 5 ሺ ህፃናት የልብ ህክምና ሰጥቷል።

ምንጭ:- ኢዜአ

እውነት በአቶ አንዳርጋቸው ይሁንታ ግብፅ ተስማማች ?

በውጭ ጉዳይ ሚንስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው የኢትዮጵያ መንግስት የልዑካን ቡድን አባላት በአባይጉዳይ የመንግስትን አቋም ለአሜሪካ መንግስት ለማስረዳት ከግብፅ እና ከሱዳን አቻዎቻቸው ጋር እዚህዋሽንግተን ዲስ ተጠርተው መምጣታቸው ይታወቃል::

በታጠረ ሚዲያ አሰራር አሁንም ድረስ የሚያምነው የዶር አብይ አገዛዝ ታዲያ በዋሽንግተን ዲሲ ኢምባሲውበኩል ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ስለአባይ ጉዳይ ለመደራደር የመጡት የመንግስት ባለስልጣናት በጋዜጠኞችበነፃነት እንዳይጠየቁ ውስን የሚዲያ ተቋማትን እና ዲጄዎችን ብቻ  መጋበዙ ብዙዎችን አስገርሟል:: ድንቄምለዉጥ እና መደመር እንዲሉ!!

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ተለይተው የተጋበዙት የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ ጋዜጠኛ ሰለሞን አባተ ለኢቲቪ የእጅአዙር ወኪል ሆና በኢምባሲው ውስጥ የምትሰራው ንጋት በቃና እና አንድ የፌስቡክ ዲጄ እንዲሁም ጥቂቶችበውስጥ የተመረጡ ብቻ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል::

በተረኛ አገዛዝ ሰዎች እንደሚዘወር የሚነገርለት በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ አምባሳደር ፍፁም አረጋየጠቅላይ ሚንስትሩ የፕሬስ ሀላፊ ሆነው በመስራታቸው ስለሚዲያ አሰራር ያውቃሉ ተብሎ ቢገመተም“ለውጡን ”አሜን ብሎ የተቀበለውን ኢሳትን እንኳ አለመጋበዛቸው አሁንም ከፍርሀት ኮፈን ያልተላቀቁ እና አቅመ ቢስ መሆናቸውን አስመስክረዋል::አይ መደመር! አይ ፍልስፍና ! “ማሞ ሌላ !መታወቂያው ሌላ ! ” አሉ የአራዳ ልጆች!!ይሰማዎታል ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር?

በጋዜጠኛ ምናላቸው ስማቸው

የጃዋር አስገራሚ ታሪክ ከዱመና ደሳሳ ጎጆ እስከ አሜሪካ እና ቦሌ ቅንጡ ቤት

ጃዋር ማን ነው ጃዋር ከትንሿ ከተማ ዱሙጋ የተወለደው በ 1986 አ.ኤ,አ የተወለደ ጃዋር እናቱ ኦርቶዶክስ አባቱ ደግሞ ሙስሊምመሆናቸው 90% ሙስሊም በሆነባት ዱሙጋ የተለያዩ ሀይማኖት የሚከተሉ ሰዎች መጋባት ያልተለመደ ድርጊትስለነበር ጃዋር በጊዜው ልዩ አድርጎት ነበር ።

 መደበኛ ትምህርቱን በ አሰላ ጀመረ ከዛም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ናዝሬት(አዳማ) ተማረ ከዛ በኋላ ነውየራሴን ማንነት እንዳውቅ ረድቶኛል ካለው ዩንቨርስቲ  “united world college of south east Asia” ከዛም Stanford university ፖለቲካል ሳይንስ አጠና ። በዚህም ወቅት ነበር በ 2006 አ.ኤ.አ የዛሬው ጃዋር ተወለደ ወደ አክትቪዝሙተቀላቀለ በ 2006 እ.ኤ.አ ለብዙ ኦሮሞ ወጣቶች ማህበር እንደ ዣንጥላ ይሆናል ያለውን አለምአቀፋዊ የ ኦሮሞወጣቶች ማህበርን (IOYA) መሰረት ።

በጊዜውም በ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ሚፅፋቸው ፅሁፎች እና በሚናገራቸው ሀሳቦች በውጭ በሚኖረውኢትዮጵያዊ ተሰሚነቱ እየጨመረ መጣ በጊዜው የ ኦነግን (OLF) አካሄድ የ ኦሮሞ ጥቅሞችን አያስጠብቅም ብሎይተች ነበር ከነዚህ ፁሁፎች “Failure to Deliver: The Journey of the Oromo Liberation Front in the Last Two Decades” አንዱ ነበር  ።

 ጃዋር አክቲቪስት ሁኖ በመጣበት ጊዜ OLF  ያለ መሪ የቀረበት ፣ ኦሮሞም ” የተበታተነበት” ጊዜ ነበር ይህ ወቅትሀሳቡን ህዝቡ በሚረዳው መልኩ ያቀረበበት እንዲሁም ወጣቱን ለ አዲስ ትግል(ለ አዲስ የ ኦሮሞ ተቃውሞፖለቲካ) ያነሳሳበት ጊዜ ነበር ይህ ወቅት ለአሁኑ ጃዋር ወርቃማ ዘመን ነበር ።

ጃዋር በትግሉ የነበረው አስተዋጽኦ : ጃዋር የቄሮን ትግል በመምራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ነበረው ለውጡም ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅአድርጓል ። ለውጡም አሁን ያለውም የኢትዮጵያ ፖለቲካ ያለ ጃዋር መመልከት ፈፅሞ አይቻልም ። 

ጃዋር አሁን ፣ 

የ OMN ዳይሬክተር እና ከ 1.7 ሚሊዮን በላይ ተከታይ ባሉት የፌስቡክ  ገፁ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ቀጥተኛም ሆነበተዘዋዋሪ እየተሳተፈ ከሚገኙ ሰዎች አንዱ (ዋነኛ ) በመሆን ተጽዕኖ ፈጣሪ ሆኖ ይገኛል ። ነገርግን ከቅርብ ጊዜወዲህ ቄሮን እንደፈለገ መንዳት ባለመቻሉ የሱ አስተዋጽኦ እየቀነሰ ይገኛል ። አሁን ላይ የድሮ ሀይሉን ለመመለስከዚህ በፊት ሲጠቀምባቸው የነበሩ ስልቶችን እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦችንና ሀይሎችን በመጨመርእየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። 

የጃዋር ባህሪ :ጃዋር በባህሪው ሀሳቡን በነፃነት መናገር የሚወድ ነው በአንድ ቃለመጠይቅ በማንነቱ ደህንነት እንደማይሰማውእና በ self confidence አለመኖሩን ከ ፖለቲካው እና ከ ኦሮሞ ማህበራት ለሁለት አመት ርቆ እንደነበር ይናገራል ። 

የጃዋር ቅንጡ ቪላ ከጃዋር መሀመድ ቅንጡ ህይወት ጀርባ ያሉ ሚስጥሮች እነሆ! የደህንነት ካሜራ የተገጠመለት 300 ካሬ እጅግዘመናዊ ቪላ ቤት በአዲስ አበባ።እያንዳንዳቸው 10 ሚለዮን ብር የሚያወጡ 3 መኪኖች!! እስከ አፍንጫቸው የታጠቁ 10 ጠባቂዎች!! 5 ምግብአብሳዮች!!

በርካቶች ይህን የጃዋር ቅንጡ ህይወት ከሳውዲ ንጉስ ጋር አመሳስለውታል፡፡ጀዋር በቅርብ ቃለምልለሱ እኔም አብይም በv8 መኪና ነው የምንሄደው ማለቱ ይተወሳል፡፡

ጃዋር በአሁኑ ግዜ የጃዋር ታሪክ ለብዙዎቻችን እንደ ማነቃቂያ ነው ። እሱ በውሸት ታሪክ ተመስርቶ ይህን ያህል ለውጥ ካመጣ እኛበዕውነተኛ ማስረጃዎች እሱን ለህግ ማቅረብ አያቅተንም የሚሉ ኢትዮጵያውያን ከዳር ዳር ተነስተዋል ::

የዛሬ ዋና ዋና ሰበር ዜናዎች

የዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 27/2012 የዋዜማ ዐበይት ዜናዎች ጤና ጥበቃ ሚንስትር ዶ/ር አሚር አማን ከሥልጣን ሊለቁ እንደሆነ አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡ ከስልጣንየሚነሱት ቦታው ለድርጅት ወይም ብሄር ውክልና ስለተፈለገ እንደሆነ ተገምቷል፡፡ አሚር በሚንስትርነትየተሾሙት ሃች አምና በሚያዚያ ወር ሲሆን፣ በሥራቸው አድናቆትን አትርፈዋል፡፡

2.በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሃሳብ እና ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብቶችን የሚከታተሉት ልዩራፖርተር በኢትዮጵያ ጉብኝት ያደርጋሉ፡፡ የልዩ ራፖርተር ዴቪድ ኬይን ጉብኝት ከኅዳር 22-29 እንደሚዘልቅቢሯቸው ባሰራጨው መረጃ ጠቁሟል፡፡ በቆይታቸው ከመንግሥት ሃላፊዎች፣ ጋዜጠኞች፣ መብት ተሟጋቾች እናሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር በሀገሪቱ ስላለው ሃሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይነጋገራሉ፡፡ ማንኛውምግለሰብ በድርጅቱ ድረ ገጽ ለሰፈሩት ጥያቄዎች እስከ ኅዳርአድራሻ መልስ እንዲሰጥም ጥሪ አድርጓል፡፡ ራፖርተሩየጉብኝታቸውን ውጤት በመጭው ሰኔ ለተመድ ሰብዓዊ መብት ካውንስል ያቀርባሉ፡፡

3.  በዋሽንግተን ውይይት የተቀመጡት የኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች እስከ ጥር 6 የሕዳሴ ግድብ የቴክኒክ ውይይትን ለማጠናቀቅ እና ፍትሃዊ ስምምነት ላይ መድረስ ተስማምተናል ሲሉ መግለጫአውጥተዋል፡፡ ስምነት ካልደረሱ ግን የ2008ቱ Declaration of Principles አንቀጽ 10 ሥራ ላይእንዲውልተስማምተዋል፡፡ “ሀገራቱ በመግለጫው አተረጓጎም ወይም አተገባበር ላይ ያላቸውን ልዩነት በወይይት ወይምድርድር ይፈታሉ፤ ካልተስማሙ አደራዳሪ ሊጠይቁ ወይም ወደ መሪዎች ጉባዔ ሊመሩት ይችላሉ”- ይላል አንቀጹ፡፡በቀጣይ የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባዎች አሜሪካና ዐለም ባንክ በታዛቢነት ይገኛሉ፡፡ ሚንስትሮቹ ኅዳር 29 እና ጥር 4 ድጋሚ በዋሽንግተን ይሰበሰባሉ፡፡

4.  ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ሕዝበ ውሳኔ ድምጽ ሰጭዎችን ምዝግባ ዛሬ ጀምሬያለሁ ብሏል፡፡ ምዝገባውበሲዳማ ዞን እና ሐዋሳ ከተማ በ1 ሺህ 692 ድምጽ መስጫ ጣቢያዎች እየተካሄደ ነው፡፡ በሀዋሳና አካባቢዋ ብቻ225 ጣቢያዎች ተዘጋጅተዋል፡፡ ምዝገባው እስከ ሕዳር 6 ይቆያል፡፡

5. ንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር ላኪዎች የተቀመጠላቸውን የሕግ አግባብ ብቻ እንዲከተሉ የሚያስገድድመመሪያ እንደሚያወጣ ሪፖርተር ዘግቧል፡፡ መንግሥት የወጭ ንግዱን ግብይት ሥርዓት ይከታተላል፡፡ ከዐለምዐቀፍ ገበያ ጋር የማይጣጣም የግበይት ሥርዓት ለወጭ ንግድ ገቢ ማሽቆልቆል ምክንያት ሆኗል፡፡ የውጭምንዛሬ ለማግኘት ሲሉ ምርታቸውን በርካሽ የሚሸጡ እና የከሰሩ አስመስለው ለመንግሥት ሪፖርትየሚያደርጉም ነጋዴዎች አሉ፡፡

6. ወርቅነህ ገበየሁ የኢጋድ ዋና ጸሃፊነቱን ዛሬ በይፋ ከተሰናባቹ ዋና ጸሃፊ ከኬንያዊው አምባሳደር ሙሀቡብማሊም መረከባቸው ታውቋል፡፡ መረጃውን ዛሬ ከቀትር በኋላ በትዊተር ገጻቸው ያሰፈሩት፣ የኢጋድ ከፍተኛ የሥራሃላፊ የሆኑት ኑር ሞሐመድ ሺክ ናቸው፡፡

7. የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር እና የተቀዋሚ መሪ ሬክ ማቻር በኡጋንዳው ለዝግ ውይይትመቀመጣቸውን ዴይሊ ሞኒተር አስነብቧል፡፡ አምና በመስከረም በፈረሙት ሰላም ስምምነት መሠረት እስከ ኅዳር12 የአንድነት ሽግግር መንግሥት መመስረት አለበት፡፡ ሆኖም የጋራ ጦር ሠራዊት ምስረታ እና የክልሎች ወሰንአጨቃጫቂ ሆነዋል፡፡ የሱዳንና የኬንያ ተወካዮች በውይይቱ ይገኛሉ፤ ኢትዮጵያ ተወካይ ስለመላኳ አልታወቀም፡፡ 

የአይሮፕላን ካፒቴን በሰራው ስህተት አየር ላይ ተሳፋሪዎችን አሸበረ

በስህተት ‘አውሮፕላኑ ተጠልፏል’ የሚለውን የአደጋ ጊዜ ጥሪ የተጫነው አብራሪ በአምስተርዳሙ የስኪፖልአውሮፕላን ማረፊያ ሽብር ፈጥሯል።የኔዘርላንድስ ፖሊስ ረቡዕ ማታ 3፡30 ገደማ አንድ አጠራጣሪ ጉዳይ ስለገጠማቸው አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ምርመራ እያካሄዱ መሆኑን በትዊተር ገፃቸው አሳውቀው ነበር።

በአውሮፓ እጅግ ሥራ ብዙ ከሆኑ አውሮፕላን ማረፊያዎች አንዱ የሆነው ስኪፖል የተወሰነ ክፍል ተዘግቶ ፖሊስምርመራ ማካሄድ ጀምሮ ነበር።ከአንድ ሰዓት በኋላ ግን አንድ አውሮፕላን አብራሪ በስህተት የተጠልፊያለሁ ቁልፍን በመጫኑ ነው ሁከትየተፈጠረው ሲል ፖሊስ ይፋ አድርጓል።

ከአምስተርዳም ወደ ስፔን ዋና ከተማ ማድሪድ ሊበር እየተዘጋጀ የነበረው አውሮፕላን አብራሪ የተጫነው ቁልፍጠላፊዎች አውሮፕላን ውስጥ ገብተዋል የሚል ምልክት የሚሰጥ ነው።ፖሊስ ሁሉንም ተሣፋሪዎች እና የበረራ ሠራተኞች ከአውሮፕላኑ በጥንቃቄ ካስወጣ በኋላ ሁሉም ሰላምመሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል።

ማኅበራዊ ሚድያ ላይ የተሰራጩ ፎቶዎች መንገደኞች ጥግ ጥግ ይዘው መረጃ ሲጠባበቁ ያሳያሉ። ቢሆንምበሌላው የአውሮፕላን ማረፊያው ክፍል መደበኛ ሥራ እየተከወነ ነበር። በአደጋ ጊዜ ጥሪው ምክንያት ለጊዜውበረራቸው የተስተጓጎለ መንገደኞችም ነበሩ።

ግርገሩ መሃል የነበረው የ38 ዓመቱ ሮቤርቶ ካሬራ «ፓይለቱ የሆነ ነገር እንዳጋጠመው ጠቆመን» ሲልየተፈጠረውን ለቢቢሲ በስልክ አስረድቷል። ከዚያም አንድ ጥግ ላይ ተወስደው ሁኔታው እኪረጋጋ ድረስ ቢያንስለአንድ ሰዓት ያህል እንደቆዩ ይናገራል። ምንም እንኳ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ እና ፖሊስ እያጣራ እንዳለ በግልፅቢታይም ሁኔታዎች የተረጋጉ ነበሩ ተብሏል

ሰበር ዜና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ህብረት አስቸኳይ መግለጫ

የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓለም አደባባዮች የሃፍረት ሸማ እንዲላበስ ተደርጓል።የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄሕብረት የኢትዮጵያ ሕዝብ በዓለም አደባባዮች የሃፍረት ሸማ እንዲላበስ ተደርጓል ሲል የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄሕብረት አስታወቀ።

ሕብረቱ “በማራቶን ደጋግመን ያሸነፍነውን ያህል፣ ሰሞኑን በጭካኔ ሬከርድ ሰብረናል!” በሚል ርዕስ ሰሞኑንበኦሮሚያ ክልል ተከስቶ ከ80 በላይ የሚሆኑ ንጹሃን ዜጎችን በአሰቃቂ ሁኔታ የቀጠፈውን ክስተት አስመልክቶመግለጫ አውጥቷል።

ሕብረቱ ለኢትዮ 360 በላከው መግለጫ እንዳለው ኢትዮጵያ ሃገራችን ፈታኝ ወቅት ላይ ትገኛለች።ሕወሃትን ለማውረድ ብዙ መስዋእትነት የተከፈለበት ለውጥም በመቀልበስ ላይ መሆኑ ሃሜት ሳይሆን ሃቅ ነውብሏል ሕብረቱ በመግለጫው።

ጁሃር መሃመድ ጥበቃዬ ሊነሳ ነው ድረሱልኝ ብሎ በደረቅ ለሊት ለተከታዮቹ ያደረገው ጥሪ ንፁህና ሰላማዊኢትዮጵያዊ ወገኖቻችን እንደበግ በገጀራና በቆርቆሮ እንዲታረዱ፣ ቤንዚን ተርከፍክፎ እንዲቃጠሉ፤ በድንጋይእንደእባብ ተቀጥቅጠው እንዲገደሉ ምክንያት ሆኗል ይላል።

የጀዋር መሐመድ ተከታዮች የገደሏቸው በአብዛኛው “ነፍጠኛ” ከሚሉት የአማራ ወገን ቢሆኑም ይላልመግለጫው ከጋሞ፣ ከጉራጌ እና ከዶርዜ ማህበረሰብ፣ እንዲሁም ሙስሊምም ክርስቲያንም ይገኙበታል ሲልያስቀምጣል።–ቀሳውስት ታርደዋል፣ ቤተክርስቲያንና መስጊድ፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የንግድ ተቋማትመቃጠላቸውም እንዲሁ።

ሕብረቱ የተከሰተው ጭካኔ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ ድንጋጤ ላይ ጥሎት ከርሟል ብሏል።ትናንት በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የሰላም የኖቤል ሽልማት ማሸነፍ አገራችን በዓለም ጋዜጦችበአድናቆት ሲዘገብላት እኛ ኢትዮያውያኖች በያለንበት አንገታችንን ቀና አድርገን የነበርነውን ያህል ሰሞኑንበተከሰተው ጭካኔ ደግሞ አንገታችንን እንድንደፋ ተደርገናል ሲል ይናገራል። 

ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብም በቀየው በተከሰተው ኢሰብአዊ ድርጊት ከሌላው ወገኑ ጋር እንደተሸማቀቀና በእጅጉእንዳዘነ የሚያከራክር ጉዳይ አይደለም ሲል ተናግሯል።

 አንድ መረሳት የሌበትና ሊሰመርበት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር ይላል ንቅናቄው በመግለጫው የኢትዮጵያ ሕዝብትናንት የልጆቹን ደም ገብሮ ሕወሃትን ያስወገደው የባሰ ዘመን ለማስተናገድ አይደለም። 

ሌላው አሳዛኝና አሳፋሪ ክስተት ደግሞ ይላል ሕብረቱ የወገኖቻችን እልቂት ሳይቆምና እሬሳቸው ስይነሳ፣የአንዳንድ ድርጅት መሪዎች ጀዋር መሐመድን በቪላው ውስጥ ተገኝተው እጅ ሲነሱትና ሲያባብሉት ማየትነው።

ሕብረቱ አሁንም ቢሆን ይላል ሕዝብን በማበጣበጥ ሕግ የሚጥሱትን መንግሥት ፈጥኖ በመያዝ ሕጋዊእርምጃ እንዲወሰድባቸው ካላደረገ የዜጎቹን ክብርና እምነት ያጣል።- ሌሎች ሕግ እንዳያከብሩ ያበረታታል ሲልገልጿል። 

ሕዝብ ለመንግሥት ሃላፊነት የሰጠው ከሁሉም በላይ የሕግን የበላይነት እዲያስከብርለት ነው። ስለዚህአጥፌዎች ያላቸው ጡንቻ ተፈርቶ ፍትህ መዘግየትና መጓደል የለባትም ሲልም ያስጠነቅቃል የኢትዮጵያሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት ። 

ስለሆነም በአሁኑ ሰዓት መንግሥት ጀዋር መሐመድንና ሕዝቡን የፈጁትን ተከታዮቹን ለቃቅሞ ለፍርድከማቅረብ ሌላ አማራጭ የለውም ብሏል መግለጫው።

 እንዲሁም በየጊዜው ከፋፋይ ዘር ተኮር መልዕክቶችን በማስተጋባት ሕዝቡን ለማናቆር በስፋት ቅስቀሳየሚያደርጉትን አቶ በቀለ ገርባን፣ ሕዝቅኤል ጋቢሳን፣ ፀጋዬ አራርሳን፣ “ፕሮፌሰር” ገመቹን መንግሥት በሕግአብሮ ተጣያቂ እንዲያደርጋቸው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት በመግለጫው አሳስቧል። 

ሊሰመርበት የሚገባው ሕዝቡ በማንነቱ ምክንያት ካደገበት ቀዬው መፈናቀል አንገፍግፎታል፤ በየጊዜውመታረድ በቅቶታል። በማንነቱ ምክንያት በቡራዩ፣ በናዝሬት፣ በአምቦ፣ በዶዶላ፣ በሰበታ በሲዳማ እና በሌሎችምየሃገሪቱ ክፍሎች የታረደው ህዝብ ዛሬ ላይ መንግሥት ይደርስልኛል በሚል እሳቤ እንደገና በዝምታ የሚታረድአይደለም ይላል ሕብረቱ። 

ሕዝቡ በሚመስለውና በእጁ ባለው እራሱን መከላከል ከጀመረ አሸናፊው በውል የማይለይና ማቆሚያ የሌለውእልቂት ሊከሰት ይችላል ሲል ሕብረቱ ስጋቱን ገልጿል።

ይህ ቃል ካልተጠበቀና ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው ካልቀረቡ ሕዝቡ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ያለው እምነትበይበልጥ እየተሸረሸረ ከመሄዱም በላይ በወገንተኛነት እንዳይፈርጃቸው ሊያግደው የሚችል ምክንያት ሊኖርአይችልም።-ስለዚህ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ የሚመለከተው አካል አስቸኳይ የሚባለውን ርምጃ ወስደውሃገሪቱን የማረጋጋት ሃላፊነት አለባቸው ብሏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ንቅናቄ ሕብረት በመግለጫው ማጠቃለያ ለሞቱና ለተጎዱ ቤተሰቦች መጽናናትንተመኝቶ፣ ፍትህ ለታረዱ ወገኖቻችን ይሁን ሲል ጥሪውን አቅርቧል።

ሰበር ዜና ዶናልድ ትራንፕ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተወያዩ

ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋርም የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጅነር ስለሺበቀለን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ መንግስት ልኡካን ዛሬ አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ገብተዋል።

በዋሽንግተን ዲሲ በሚካሄደው ውይይት ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያላትን አቋም እንደምታስረዳ ከውጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም በሰጠው መረጃ፥ የህዳሴ ግድብን በተመለከተ አሜሪካ ያቀረበችውየአወያይነት ሚና የኢትዮጵያን የቀደመ አቋም የማያስቀይር መሆኑን መግለፁ ይታወሳል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ገዱ ከፕሬዝዳንት ትረምፕ ጋር እየተወያዩ መሆናቸውን ዶናልድትራንፕ በቲዊተር ገፃቸው ዘግበዋል አዲስ ሚድያ ኔትወርክ ጥቅምት 26 የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶገዱ አንዳርጋቸው ከሱዳንና ከግብጽ አቻዎቻቸው ጋር በመሆን በነጩ ቤተ መንግስት ከፕሬዝዳንት ዶናልድትረምፕ ጋር እየተወያዩ ነው።

ከዚህ በመቀጠልም የሶስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ የአሜሪካ የገንዘብ ተቋም ኃላፊ ስቴቨን መንቺንእና የአለም ባንክ ፕሬዝዳንት በተገኙበት በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ። በዚህ ውይይት ላይምየኢፌዴሪ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ስለሺ በቀለ እንደሚሳተፉ በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

የተሰረቀ ሞባይል መግዛት ያመጣው አስከፊ መዘዝ

ሰላም እንዴት ናችሁ ውድ የፌስቡክ ገጽ ተከታዮቻችን “እንደዋዛ” በተሰኘው ፕሮግራማችን ብዙውን ጊዜ ችላ የምንላቸው፤ ነገር ግን ወንጀል ሆነው በህግ ማህደሮቻችን ላይ ሊያስጠይቁ እንደሚችሉ የተቀመጡ ጉዳዮችን የምናይበት ፕሮግራም ነው፡፡

ዛሬም እንደተለመደው በስርቆት የተገኘን ሞባይል በርካሽ መግዛት በወንጀል ሊያስጠይቅዎ እንዲሁም እስከ 1 ዓመት በሚደርስ እሥራት ሊያስቀጣዎ እንደሚችል ያውቃሉ? በሚል አርዕስት ላይ ተከታዩን አጭር ጹሁፍ ልናስነብባችሁ ወደናል መልካም ንባብ፡፡መቸም ሰው ነንና በሒዎት ውጣ ውረዶች ውስጥ የተለያዩ ፍላጎቶች ይኖሩናል፤

በዚህም መካከል አንዳንድ ጊዜ በንግድ ሱቆች ላይ ከህጋዊ የግብይት ስርዓት ውጭ አንዳንድ ሰዎች የሞባይል ስርቆት ወንጀል በመፈጸም የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት ሲሉ የሰረቁትን ውድ ሞባይል ለሌላ ሰው በርካሽ ዋጋ አሳልፈው ሲሸጡ ይስተዋላል፤ ነገር ግን በህግ ማህደሮቻችን ላይ ከሻጭ በተጨማሪ ገዥም ወንጀለኛ እንደሆነ ተቀምጧል መቸስ “ሕግን አለማወቅ ከተጠያቂነት አያድንም!” አይደል የሚባለው ለማንኛውም ተከታዩ ጥንቅር ህጋዊ አንድምታውን ያስቃኘናል፡-

ከመደበኛ የግብይት ሥርዓት ውጭ በስርቆት የተገኝን ሞባይል በተለያዩ አጋጣሚዎች ከግለሰቦች በርካሽ ዋጋ የምንሸምታቸው የሞባይል ስልኮች ፍርድ ቤት አስቀርበው በእሥራት ሊያስቀጡን የሚችሉበት አጋጣሚ ጥቂት አይደለም፡፡

የመሸሸግ ወንጀልን የሚደነግገው የተሻሻለው የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 682 የወንጀል ፍሬ ወይም ውጤት የሆኑ ንብረቶችን መያዝ፣ መደበቅ፣ ማስቀመጥ ሊያስከትል የሚችለውን ኃላፊነት ይዘረዝራል፡፡

በዚህ ድንጋጌ መሠረት ወንጀለኞችን ለመረዳት ወይም ከወንጀል ድርጊቶች ጥቅም ለማግኘት ታስቦ/ታውቆ ከሚደረግ የመሸሸግ ድርጊት በተጨማሪ ግለሰቦች በቸልተኝነት ማለትም የተጠቀሰው ንብረት የወንጀል ፍሬ መሆኑን ማወቅ እየተገባቸው በግድ የለሽነት ወይም በሌላ ምክንያት ይዘው የሚገኙ ሰዎች የሚቀጡበትን አግባብ ያስቀምጣል፡፡

በዚህም መሠረት ግለሰቦች በተለያየ አጋጣሚ እጃቸው የገቡ ንብረቶች በወንጀል ምክንያት ከትክክለኛ ባለቤቶቻቸው የተወሰዱ መሆኑ ሲረጋገጥ እስከ 1 ዓመት በሚደርስ እሥራት ሊያስቀጡ ይችላሉ፡፡

በመሆኑም ጎጃም በረንዳ ወይም ከሰፈር ወጠምሾች መንገድ ላይ የገዙ ሞባይል የስርቆት ወይም ሌላ የወንጀል ፍሬ መሆኑ ከተረጋገጠ እርሶንም ሊያስጠይቆት ይችላል፡፡

የተሰረቀ መሆኑን አላውቅም ነበር ብለው የሚያቀርቡት መከላከያም ከገዙበት ዋጋና ሁኔታ ጋር ተያይዞ የሚታይና የሚመዘን በመሆኑ ለምሳሌ በመደበኛ ሁኔታ ሊያወጣ ከሚችለው ዋጋ በጣም ዝቅ ባለ መጠን ንብረቱን መሸመትዎ፣ ግብይቱን ሲያካሒዱ በጨለማ ከሰው ተደብቀው መሆኑ …ወዘተ በርግጥም የተሰረቀ ንብረት መሆኑን ያውቁ እንደነበር የሚያመላክቱ ፍሬ ነገሮች ተደርገው ሊወሰዱ ይችላሉ፡፡

ስለሆነም የተገዛው ዕቃ ከላይ በተመለከቱት ምክንያቶች ከትክክለኛ ባለቤት መገዛቱ ካልተረጋገጠ ርስዎን ሊያስወነጅልዎት ስለሚችል ዕቃን በርካሽ ዋጋ አገኘሁ ብሎው ለመግዛት እንዳይቻኮሉ አጥብቀን ልንመክርዎ እንወዳለን፡፡

ውድ አንባቢያን ለዛሬ ያዘጋጀንላችሁን ጥንቅር በዚሁ አበቃን በቀጣይ በሌላ ፕሮግራም እስክንገናኝ መልካም ጊዜን ተመኘን፡፡መረጃውን ያገኘነው ከአቢሲኒያ ለው ድህረ-ገጽ ላይ ነው ሰላም፡፡