ሰበር መረጃ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡጁንቡራ ላይ በአሸባሪ ችግር ገጠመው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቡጁምቡራ በአሸባሪነት በተጠረጠረ ግለሰብ ችግር ገጠመው በቡጁምቡራ ያረፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላንአንድ ተሳፋሪ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት በሰነዘረው ማስፈራሪያ አውሮፕላኑ ወታደራዊአውሮፕላኖች ወደሚያርፉበት የቡጁምቡራ አየር ማረፊያ እንዲቆም መደረጉ ተነገረ።

አውሮፕላኑ ዛሬ በቀጥታ በረራ ከአዲስ አበባ ወደ ቡሩንዲ ዋና ከተማ ቡጁምቡራ እየበረረ ሳለ ነበር ችግሩየተከሰተው ተብሏል።

ቢቢሲ ስማቸው እንዳይጠቀስ ከጠየቁ የአየር መንገዱ ሰራተኛ ለማረጋገጥ እንደቻለው የተባለው ችግርእንዳጋጠመና ምንም ጉዳት ሳይደርስ ቡጁምቡራ አርፏል።

ቢቢሲ ክስተቱን በተመለከተ ለማጣራት ወደ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮሚዩኒኬሽን ክፍል ደውሎ ጥያቄቢያቀርብም የተሰጠው ምላሽ ስለጉዳዩ በአጭር ጊዜ ውስጥ መግለጫ እንደሚሰጥ ብቻ ነው።

ነገር ግን መረጃ የተጠየቁት የአየር ባልደረባ ስለክስተቱ ማብራሪያ ከመስጠት ተቆጥበው ማረጋገጫም ሆነማስተባበያ ለመስጠት አልፈቀዱም።

ክስተቱን በተመለከተ ለቢቢሲ ያረጋገጡት የአየር መንገዱ ባልደረባ እንደሚሉት ከሆነ “አውሮፕላኑ በአየርማረፊያው ወታደራዊ ክፍል ውስጥ እንዲያርፍ ተደርጎ ችግሩን የፈጠረው ግለሰብም በቁጥጥር ስር ውሏል።”

ቢቢሲ ከተጓዦቹ አንዱን በማነጋገር እንዳረጋገጠው ክስተቱ ተሳፋሪዎች ላይ ጭንቀት ፈጥሮ ነበር።

ነገር ግን በአውሮፕላኑ ውስጥ ያጋጠመውን ችግር የፈጠረው ግለሰብ ፍላጎቱ ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀነገር የለም።

የቡሩንዲ የደህንነት መስሪያ ቤት በትዊተር ገጹ ላይ ስለክስተቱ ጠቅሶ በሽብር ድርጊት የተጠረጠረው ግለሰብምበቁጥጥር ስር መዋሉን አመልክቷል።

ክስተቱን በተመለከተ ቢቢሲ ያገኘውና እስካሁን በሁለተኛ ወገን ያልተረጋገጠው መረጃ እንደሚያመለክተውግለሰቡ በአውሮፕላኑ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ገብቶ በመዝጋት አውሮፕላኑን እንደሚያፈነዳው በመግለጽበማስፈራራቱ ችግሩ መከሰቱ አመልክቷል።

ከዚህ አንጻር ለቢቢሲ የተናገሩት የአየር መንገዱ ባልደረባ ክስተቱ በሰላም መጠናቀቁንና በተሳፋሪዎችም ሆነበአውሮፕላኑ ላይ ምንም ጉዳት አለመድረሱን ገልጸዋል።

በእርግጥ ግለሰቡ እንዳለው የሚፈነዳ ነገር ይዞ እንደነበረ የሚያመለክት ነገር ያልተገኘ ሲሆን፤ ለፈጸመውድርጊትም ምክንያቱ ምን እንደሆነ እስካሁን ምንም የታወቀ ነገር የለም።

አውሮፕላኑ ምን ያህል ተጓዦችን አሳፍሮ እንደነበረና ችግሩ የተከሰተው ለማረፍ በተቃረበበት ይሁን ወይም በጉዞላይ እንዳለ አልታወቀም።

ክስተቱን ተከትሎ አውሮፕላኑ በአየር ማረፊያው ውስጥ በሚገኝ የወታደራዊ አውሮፕላኖች ማቆሚያ ክፍልእንዲቆይ እንደተደረገ ምንጮች ከቡጁምቡራ አመልክተዋል።

ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና ለጤና ጠቃሚው የቱ ነው

ልጅቱ ሁልጊዜ እየመጣች ታማርራለች፡፡ኑሮ አልተሳካልኝም፣ አልሞላልኝም፣ ባሌ ያስቸግረኛል፣ ሥራ ቦታ ሰላም የለኝም፣ ጎረቤቶቼ ረበሹኝ፣ ሕመሙ በረታብኝ፣ ገንዘቤ አልበረክት አለ፤ ጓደኞቼ ያሙኛል፣ ልጆቼ ይበጠብጡኛል፡፡ ስለ ሸረኛ፣ ስለ መጋኛ፣ ስለ ምቀኛ፣ ስለ መተተኛ የማትለው ነገር የላትም፡፡ አባቷ የተለያዩ ታሪኮችን እየጠቀሰ ሊመክራት፣ ሊያጽናናትና ሊያበረታት ሞከረ፡፡ እርሷ ግን ማማረሯን፣ መማረሯንም አላቆመቺም፡፡ እንዲያውም ምሬቷ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ፤ ኑሮዋንም እየጠላቺው፣ ፈተናዋንም እየፈራቺው መጣች፡፡

አንድ ቀን መኖር አስጠልቷት፣ ችግሩና መከራም በርትቶባት፣ ምሬቷም ጫፍ ደርሶ መጣች፡፡ ‹‹በቃ ከዚህ በኋላ መኖር አልፈልግም፤ ይህንን ያህልስ እኔ ለምን እፈተናለሁ፤ ለምንስ ችግር ይበረታብኛል፤ ለምንስ ሁሉም ነገሮች ይጠሙብኛል፤ በቃ እኔ መኖር የለብኝም›› እያለች ታለቅስ ነበር፡፡አባቷ ምክሩ ሁሉ እንዳልሠራ፣ የነገራትንም ሁሉ እንደዘነጋቺው ተረዳ፡፡‹‹ተከተይኝ›› አላትና ወደ ማዕድ ቤት ገቡ፡፡

ወንበር ሰጣትና እርሱ ወደ ምግብ ማብሰያው ሄደ፡፡ ኮመዲኖውን ከፈተና ዕንቁላል፣ ድንችና የተፈጨ ቡና ይዞ መጣ፡፡ እርሷ ግን ትዕግሥቷ አልቆ ነበር፡፡ በልቧም ‹‹እኔ ኑሮ መርሮኝ እርሱ ምግብ ሊጋብዘኝ ይፈልጋል›› ትል ነበር፡፡ ‹‹አባቴ ችግሬን አልተረዳውም ማት ነው፤ ርቦኝ የተነጫነጭኩ መሰለው›› አለች፡፡ ‹‹እኔ ምግብ አልፈልግም፣ ቡናም አልጠጣም፤ በቃ እንዲያውም እሄዳለሁ›› አለችው፡፡ ዝም አላት፡፡

ሦስቱ ምድጃዎች ላይ የሻሂ ማፍያዎችን ጣደ፡፡ በአንደኛው ላይ ዕንቁላሉን፣ በሌላው ላይ ድንቹን፣ በሦስተኛውም ላይ የተፈጨውን ቡና ጨመረው፡፡ ከዚያም ወደ ልጁ መጣና ከጎኗ ተቀመጠ፡፡ ‹‹ምን እየሠራህ ነው፤ የኔ ችግርና ምግብ ምን አገናኛቸው፤ ቤቴ ውስጥ ሞልቷልኮ፤ ሕጻን አደረግከኝ እንዴ፤ ዕድሌ ነው፣ አንተ ምን ታደርግ›› ትነጫነጫለች፣ ትቆጣለች፣ ታማርራለች፡፡ አባቷ ግን ዝም ብሎ ያዳምጣታል፡፡ ማልቀስ ጀመረች፡፡ ትከሻዋን እየደባበሰ ዝም አላት፡፡ ቃል ከአፉ አልወጣም፡፡

ውኃው መንፈቅፈቅ ጀመረ፡፡ አልፎ አልፎም ውኃው ከመክደኛው ወጥቶ እሳቱ ላይ ሲንጠባጠብ ‹ትሽ› የሚለው ድምጽ ይሰማ ነበር፡፡ አባቷ ድንገት ቆመ፡፡ ደንግጣ እንደተቀመጠች አቅንታ አየቺው፡፡ ‹‹በይ ተነሺ› አላት፡፡ ዘገም ብላ ተነሣቺ፡፡

‹‹ሦስቱንም የሻሂ ማፍያዎች ክፈቻቸው›› አላት፡፡‹‹ለምን?›› አለች ግራ ተጋብታ፡፡
‹‹ግዴለም እሺ በይኚ››መንቀር መንቀር እያለቺ ወደ ማንደጃው ሄደቺ፡፡

‹‹ሦስቱም ማፍያዎች ውስጥ ያሉትን ነገሮች አውጫቸው›› አላት፡፡ ዕንቁላሉንና ድንቹን በጭልፋ አወጣቺና ሰሐኖቻቸው ላይ አደረገቻቸው፡፡ ቡናውን ስኒ ላይ ቀዳቺው፡፡

እና ምን ይሁን?›› አለቺው ልጁ፡፡‹‹ድንቹን ተጫኚው፣ ዕንቁላሉን ላጭው፣ ቡናውንም ቅመሺውተመልከቺ፤ ድንቹ ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ጠንካራ ነበረ፡፡ የፈላው ውኃ ግን ጠንካራውን ድንች ፈረካከሰው፡፡ ዕንቁላሉ የፈላው ውኃ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ውጩ ጠንካራ ውስጡ ግን ፈሳሽና ስስ ነበረ፡፡ ውኃው ሲፈላ ግን ውስጡ ፈሳሽና ስስ የነበረው አስኳሉ ጠንካራ ሆነ፡፡ ቡናው ሲፈላ ቤቱን በመዓዛው ዐወደው፣ የአካባቢውንም ጠረን ቀየረው፤ ጣዕሙም ልዩ ሆነ፡፡

‹‹ሦስቱም በተመሳሳይ ማፍያ በተመሳሳይ ዓይነት እሳት ነበር የተጣዱት፡፡ ችሀግራቸው አንድ ነው፤ ለአንድ ዓይነት ችግር የሰጡት ምላሽ ግን የተለያየ ነው፡፡ ድንቹ ጥንካሬውን አጣ፣ ዕንቁላሉ አስኳሉ ጠነከረ፣ ቡናው መዓዛውና ጣዕሙን ይበልጥ እንዲያወጣው አደረገው፡፡ ልጄ ያንቺም ችግር ያለው ከገጠመሽ ችግርና ፈተና አይደለም፡፡ ለገጠመሽ ችግርና ፈተና ከምትሰጪው ምላሽ እንጂ፡፡ የተለያዩ ሰዎች አንድ ዓይነት ፈተና ሊገጥማቸው ይችላል፤ እንዲያውም በኑሮው ውስጥ የማይፈተን ሰው የለም፡፡ ነገር ግን ሰዎች ለችግርና ለፈተና የሚሰጡት ምላሽ የተለያየ ነው፡፡

‹‹ፈተና አንዳንዱን እንደ ድንች ጥንካሬውን አጥቶ እንዲፈረካከስ ያደርገዋል፡፡ አንዳንዱን ሰው ደግሞ እንደ ዕንቁላሉ ውስጡን ያጠነክርለታል፤ ሞራሉን ገንብቶ፣ መንፈሱን ያበረታዋል፡፡ እሳት የብረትን ዝገት እንዲያስወግድ ፈተናም የአንዳንዱን የስንፍና ዝገት ያስወግድለታል፣ ውስጡን ጠንካራ ያደርግለታል፡፡ አንዳንዱ ደግሞ ችግርና መከራው፣ ፈተናና ስቃዩ ውስጣዊ መዓዛውንና ጣዕሙን እንደ ቡናው እንዲያወጣ ያደርገዋል፡፡ ውስጣዊ ችሎታውን፣ ዕምቅ ዐቅሙን፣ የተዳፈነ ተሰጥዖውን፣ ለሌሎች ሊተርፍ የሚችል ጸጋውን ያወጣለታል፡፡

‹‹ውሳኔው በእጅሽ ላይ ነው ልጄ፤ ችግር እንዳይመጣ፣ ፈተናም እንዳይኖር፣ መከራም እንዳይገጥም ተግዳሮትም እንዳይደርስ ማድረግ አይቻልም፡፡ ራስን ወይ ድንች፣ ወይ ቡና ወይም ደግሞ ዕንቁላል ማድረግ ግን ይቻላል፡፡››

ልጁ ጉንጩን ስማው አንገቷን እየነቀነቀች ወጣች፡፡ ውስጧም ‹ዕንቁላል፣ ድንችና ቡና› ይል ነበር፡፡ ሌሎችም እንዲያነብቡት ሼር ያድርጉላቸው፡፡

ጆሮዋችሁን በጥጥ ማፅጃ ኩክ የምትጠቀሙ ሰዎች ይህን ታውቃላችሁ

አንድ ግለሰብ የጥጥ ጆሮ ማፅጃ ለረጅም ግዜ በመጠቀሙ ለአደገኛ አይምሮ ካንሰር ተጋለጠ፡፡ የ31 ዓመቱ እንግሊዛዊ የጥጥ ጆሮ ማፅጃው ለረጅም ግዜ በመጠቀሙ የጆሮ ታንቡሩን አልፎ የአይምሮ ክፍሉን ጎድቶታል ቴክ ታይምስ በድህረ ገፁ አስነበበ፡፡

የጆሮ ማፅጃው ጥጥ በጆሮ ውስጥ በመሰግሰጉ መስማት እንዳይችል እንዳደረገው እና ችግሩ ወደ አይምሮ ካንሰር መሻገሩን የሚናገረው ይህው ግለሰብ፡፡

የጭንቅላት ካንሰሩ ወደ ሚጥል በሽታ እና እራስን እሰከ መሳት ደረጃ እንዲደረሰ እንዳደረገው የገለፁት ደግሞ በእንግሊዝ የኮምንትሪ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር የሆኑት አሌክስ አንደር ካርቶም ናቸው፡፡

የዶ/ሩ የአልትራሳውንድ ምርመራ ውጤት እንዳሰረዱት የግለሰቡ ውስጠኛው የጭንቅላት ክፍል በከፍተኛ ሁኔታ መጎዳቱን አስረድተዋል፡፡

ዶ/ሩ ጨምረው እንዳሉት መጠነኛ ቀዶ ጥገና ተደርጎለት በውስጡ የቀሩት የጥጥ ቁርጥ ራጮች በማውጣት ህመምተኛውን ወደ ቀድሞ አቋሙ መመለስ እንደሚቻል አሰረድተዋል፡፡